የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/97 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 12/97 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ፦ አማርኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ። እንግሊዝኛ:- ታላቁ ሰው እና/ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ። ጥር፦ አማርኛ:- ቤተሰብ ወይም ወጣትነትህ የተባሉት መጽሐፎች (በብር 3)። እንግሊዝኛ:- በጉባኤ ያለ ማንኛውም ከ1985 በፊት የታተመ ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። የካቲት፦ አማርኛ:- ቤተሰብ ወይም ወጣትነትህ (በብር 3)። እን ግሊዝኛ:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!

◼ ጥር 5 በሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙት የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ ይሰጣቸዋል። ለልጆቻቸው ደግሞ መታወቂያ ካርዱ ይሰጣቸዋል።

◼ ከየካቲት (ቢዘገይ ከመጋቢት 1) ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “አምላክ ለሕይወት ያለው ዓይነት አመለካከት አላችሁን?” የሚል ይሆናል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ቅዳሜ ሚያዝያ 11 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የመታሰቢያ በዓል ለማክበር አመቺ ዝግጅቶችን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር ቢቻልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ጠጅ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ማዞር መጀመር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቀው በስንት ሰዓት እንደሆነ አቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር የሚመረጥ ቢሆንም ሁልጊዜ እንዲህ ማድረግ አይቻል ይሆናል። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ ምናልባት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት የሚሆን ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በበዓሉ ላይ ለመገኘት እንዳይቸገሩ የመታሰቢያው በዓል የሚጀምረው በጣም ከመሸ በኋላ መሆን የለበትም። ከበዓሉ በፊት ወይም በኋላ ከእንግዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ ፍላጎት ላሳዩ ለአንዳንዶች ቀጣይ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ለማድረግ ወይም እዚያ የተገኙት ሁሉ እርስ በርስ ማበረታቻ ለመለዋወጥ እንዳይችሉ እስከሚያደርግ ድረስ ፕሮግራሙ በጣም የተጣበበ መሆን የለበትም። ሽማግሌዎች ሁሉንም ነገር በደንብ ካጤኑ በኋላ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙት ሁሉ በአጋጣሚው ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ምን ዝግጅት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን አለባቸው።

◼ በ1998 በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሑድ መጋቢት 29 ይሰጣል። የንግግሩ አስተዋፅዖ ይላክላችኋል። በዚህ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የወረዳ ስብሰባ ወይም የልዩ ስብሰባ ቀን ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ያቀርቡታል። ማንኛውም ጉባኤ ከመጋቢት 29, 1998 በፊት ልዩ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።

◼ ጉባኤዎች የወረዳ ስብሰባና የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም በሚኖራቸው ጊዜ የሽማግሌዎች አካል የሚከተለውን ማስተካከያ ለማድረግ ንቁ መሆን ይኖርበታል:- የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም በሚደረግበት ጊዜ ጉባኤዎች በሳምንቱ ውስጥ የሚያደርጉትን የተለመዱትን ስብሰባዎች ያከናውናሉ። የሕዝባዊ ስብሰባና የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ግን ይሰረዛሉ። የወረዳ ስብሰባ በሚደረግበት ጊዜ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ስብሰባና የአገልግሎት ስብሰባ ጭምር የሚሰረዙ ሲሆን በዚያ ሳምንት የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ብቻ ይደረጋል።

◼ ጉባኤዎች የ1997⁠ን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ጥራዞችን ከታኅሣሥ የጽሑፍ ትእዛዛቸው ጋር መላክ መጀመር ይኖርባቸዋል። ጥራዞቹ በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ናቸው።

◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ታኅሣሥ 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ በ1999 የሚከበረው የመታሰቢያው በዓል የሚውለው ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። በዓሉ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው እንደመሆኑ መጠን የሽማግሌዎች አካል በመታሰቢያው በዓል ላይ ንግግር የሚሰጠውን ወንድም በሚመርጥበት ወቅት በየዓመቱ አንድ ወንድም ብቻ ከመጠቀም ወይም በየተራ ከማድረግ ይልቅ የተሻለ ብቃት ያለውን ሽማግሌ መምረጥ ይኖርበታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ