ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ላይቤሪያ፦ በሞኖሮቪያ የሚገኘው የቅርንጫፍ ቢሮ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሳቢያ ለ15 ወር ተዘግቶ ከቆየ በኋላ ከመስከረም 1 ጀምሮ እንደገና ሥራውን ጀምሯል። በመስከረም ወር 1,977 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊ ቁጥር ሪፖርት አድርገዋል።
ሞዛምቢክ፦ በመስከረም ወር 28,005 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ተመዝግቧል።
ኔፓል፦ በመስከረም ወር 306 አዲስ የአስፋፊዎች ቁጥር ተመዝግቧል። በአሁኑ ጊዜ ወደ 500 የሚጠጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እየተመሩ ነው።
ሴንት ሄሌና፦ እያንዳንዱ የደሴቲቷ ነዋሪ የመንግሥት ዜና ቁጥር 35 አንድ ቅጂ ደርሶታል።
በርካታ አገሮች የአገልግሎት ዓመቱን የጀመሩት ባለፈው ዓመት ከነበረው እስከ 5 በመቶ ጭማሪ የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር በማስመዝገብ ነው:- ሆንግ ኮንግ 4,230፤ ማዳጋስካር 8,749 (912 የደረሰ ከፍተኛ የዘወትር አቅኚዎችን ቁጥር ጨምሮ) እንዲሁም ታይዋን 3,497።