የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11 ቀን ነው። ሽማግሌዎች ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጧቸው ይገባል:-
◼ የስብሰባውን ሰዓት ስትወስኑ ቂጣና ወይኑ መዞር ያለበት ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ መሆኑን አትዘንጉ።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን መዘጋጀት ይገባዋል።—መጠበቂያ ግንብ 2-106 ገጽ 17 ተመልከት።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች እንዲሁም አመቺ የሆነ ጠረጴዛና የጠረጴዛው ልብስ ወደ መንግሥት አዳራሹ መጥተው ቀደም ብሎ በየቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹም ሆነ ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት ይገባዋል።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩት ወንድሞች ቀደም ብሎ ሊመረጡና ተገቢ ስለሆነው አሠራርና ስለተሰጣቸው የሥራ ድርሻ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል።
◼ የአካል ጉዳተኞችንና በቦታው መገኘት የማይችሉትን ቅቡዓን ለማስተናገድ ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የበዓሉ ሥርዓት በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲደረግ ታቅዶ ከሆነ በመግቢያና መውጫ አካባቢ፣ በእግረኞች መተላለፊያና በመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።