የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥቅምት 5 የሚጀምር ሳምንት
51 (127)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ለስብሰባዎች በሰዓቱ መድረስ። ሁለት ወይም ሦስት የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ወደ ስብሰባዎች ዘግይቶ መምጣትን በሚመለከት ይወያያሉ። ድንገተኛ አደጋዎች፣ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ፣ የትራፊክ መጨናነቅና እነዚህን የመሳሰሉ ያልተለመዱ ሁኔታዎች አንድን ሰው ከስብሰባ ሊያዘገዩት እንደሚችሉ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ማርፈድን ልማድ አድርገዋል። ለስብሰባዎች በሰዓቱ ለመድረስ የሚረዱ ነጥቦችን እየጠቀሱ ያብራራሉ:- (1) በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት መብታችን፣ በዚያ ለሚቀርብልን መንፈሳዊ ምግብና ላለው ሕብረት ልባዊ አድናቆት ማሳየት፣ (2) የግል ጉዳዮችን በተደራጀ መንገድ ማከናወንና ቀደም ብሎ ጥሩ እቅድ ማውጣት፣ (3) በቤተሰብ አባላት መካከል በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ትብብር ማስፈን፣ (4) ቀደም ብሎ በመውጣት ድንገት ሊያጋጥሙ ለሚችሉት ችግሮች በቂ ጊዜ እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም (5) በስብሰባው ላይ የተገኙትን ሌሎችን ላለማወክ ልባዊ የአሳቢነት ስሜት ማዳበር። ለመሻሻል ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ እንዲህ ዓይነቱን አርፍዶ የመድረስ ችግር ማስወገድ እንደሚቻል ሁሉም ይስማማሉ።
20 ደቂቃ፦ “የመጽሔት ደንበኞች በማፍራት ‘የመንግሥቱን ዘር መዝራት።’” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አንዳንዶች የመጽሔት ደንበኞችን ያገኙትና ደንበኝነቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ የቻሉት እንዴት አንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ። ከዚያም መጽሔት ሲበረከትና ቀጣዩን እትም ይዞ ለመመለስ ቀጠሮ ሲይዙ የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት
ጥቅምት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 (42)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም ሆነው የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾች—ጸሐፊ።” የጉባኤው ጸሐፊ የሥራ ኃላፊነቱን በአጭሩ በመከለስ በንግግር ያቀርበዋል። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን በጊዜው በመመለስ መተባበር እንደሚችሉ ጠበቅ አድርጎ ይገልጻል።
10 ደቂቃ፦ ሞቅ ያለ የአቅኚነት መንፈስ አላቸው። በ1998 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 104-7 ላይ የተመሠረተ አበረታች ንግግር። በጃፓን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አቅኚዎች ሊኖሩ የቻሉት ለምን እንደሆነ፣ የቤት እመቤቶች ለመንፈሳዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ እንዲሰጡ ያስቻላቸው ምን እንደሆነ፣ ሁላቸውም አቅኚ እንዲሆኑ ያነሳሳቸው ነገር ምን እንደሆነና ከአቅኚዎቹ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት እነማን እንደሆኑ አብራራ። አቅኚ የሆኑ ወላጆች የሚያሳድሩትን በጎ ተጽዕኖ ግለጽ። አንድ ሰው አቅኚ ለመሆን ሲል በሕይወቱ ውስጥ ማስተካከያ ማድረግ ምን ዓይነት ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅበት ጎላ አድርገህ ግለጽ። ሁሉም አቅኚ ለመሆን ይችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ሁኔታዎቻቸውን መለስ ብለው በቁም ነገርና በጸሎት እንዲያስቡበት አበረታታ።
20 ደቂቃ፦ “መጽሔቶችን ታነብባላችሁን?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 4፣ አንቀጽ 5-6 ላይ የሚገኙትን የግል ንባብ ፕሮግራም ለማውጣት የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦች አጠር አድርገህ ግለጽ።
46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በቅርቡ በእጃችን ከደረሱን መጽሔቶች ላይ ለውይይት የሚሆኑ ነጥቦችን ጠቁም። ከ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 45 እንዲሁም ከጥቅምት 22, 1996 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 32 ላይ የሚገኙትን ተሞክሮዎች ተናገር። ሁሉም በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሚደረገው መጽሔት በማሰራጨት ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ ለመጠበቂያ ግንብ ጥናት መዘጋጀት የሚቻልበት መንገድ። በ5–107 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13፣ አንቀጽ 16-18 እና በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 7፣ አንቀጽ 11 እንዲሁም ጥናት 18 አንቀጽ 4-6 ላይ ተመሥርቶ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ:- (1) በመጠበቂያ ግንብ ላይ ከሚወጡት ከእያንዳንዱ የጥናት ርዕሶች የተቻለውን ያህል ጥቅም ማግኘታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (2) አዲስ እትም ሲደርሰን ምን ማድረግ ይኖርብናል? (3) ለመጠበቂያ ግንብ ጥናት ለመዘጋጀት ጥሩ ዘዴ የሚሆነው ምንድን ነው? (4) በጥናቱ ውስጥ ለሰፈሩት ጥቅሶችና ለትምህርቱ ጭብጥ ምን ዓይነት ትኩረት መስጠት ይገባል? (5) የተማርናቸውን ነገሮች መከለስ የምንችለው እንዴት ነው? (6) ትምህርቱን በግል ጥናታችን ከሸፈንን በኋላ ልናሰላስልባቸው የሚገቡ ቁልፍ ነጥቦች ምንድን ናቸው? (7) ሐሳብ ለመስጠት መዘጋጀት የሚኖርብን እንዴት ነው? (8) በአንዱ ጥያቄ ላይ ብቻ የተለያዩ ሐሳቦችን መስጠት የሚቻለው እንዴት ነው? አንዳንዶች ከመጠበቂያ ግንብ ጥናት ከፍተኛ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በግላቸው ምን እንዳደረጉ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።—በተጨማሪም አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ገጽ 65-7ን ተመልከት።
መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” የሚለውን ከልስ።
20 ደቂቃ፦ “በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ አምላካዊ ታዛዥነት ማሳየት።” በሰኔ 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 26-9 ላይ የተመሠረተ ንግግር። የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላቸው አዎንታዊ አመለካከት እንዲይዙና ከጉባኤው ጋር በንቃት እንዲተባበሩ የሚያግዝ ደግነት የተላበሰ ማበረታቻና ምክር ስጥ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።