የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 (38)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የነሐሴ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት አንዳንድ ሐሳብ ስጥ። “የሚያስመሰግን ሥራ!” የሚለውን ሣጥን አንብብና ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ፦ “ሁሉም ‘ቃሉን ከልብ መቀበል’ አለባቸው!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ከሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንቀጽ 21 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን አክለህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ!” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የሚደረገው የተጠናከረ ዘመቻ በጉባኤው ውስጥ እንዴት እንደሚዘጋጅ ግለጽ። በተቻለ መጠን ተሞክሮ ያላቸው አስፋፊዎች ከአዳዲስ አስፋፊዎች ጋር እንዲሠሩ ይደረጋል። በሚያዝያ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ አንቀጽ 12–15 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ከልስ። ችሎታ ያለው አንድ አስፋፊ በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። ሁሉም አዲስ ጥናት ለማስጀመር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ አበረታታ።
መዝሙር 15 (35) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ የማበርከቱን ዘመቻ እየደገፋችሁ ነውን? የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። የጥያቄ ሣጥን።
20 ደቂቃ፦ “በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ በመስጠት አንዱ ሌላውን ያንጸው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ሐሳብ መስጠት መንፈሳዊ እድገታችንን እንዴት ሊያፋጥን እንደሚችል አብራራ። (ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 38፣ አንቀጽ 4ን ተመልከት።) አንቀጽ 3 ላይ ያለውን ምክር ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። አንዳንዶች ሐሳብ ለመስጠት ወደኋላ የማለት ስሜታቸውን እንዴት እንዳሸነፉና በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ በመስጠት በመካፈላቸው በረከት ያገኙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 64 (151)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም ሆነው የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾች—ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት የበላይ ተመልካች።” የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በንግግር ያቀርበዋል። ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ከገጽ 10–12 ከአንቀጽ 6–12 ያለውን ከልስ።
17 ደቂቃ፦ “በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ።” ከአንቀጽ 1–7 ያለውን የአባሪ ገጹን ክፍል በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በተለይ ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል ተግባራዊ በሚሆኑት ነጥቦች ላይ ትኩረት አድርግ።
መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 41 (89)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ የማበርከቱን ዘመቻ እየደገፋችሁ ነውን? የሒሳብ ሪፖርት።
25 ደቂቃ፦ “በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ።” ከአንቀጽ 8–21 ያለውን የአባሪ ገጹን ክፍል በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በተለይ ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል ተግባራዊ በሚሆኑት ነጥቦች ላይ ትኩረት አድርግ።
15 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችሁን ማሻሻል የምትችሉባቸው መንገዶች። በግንቦት 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ገጽ ከ16–17 ላይ የተመሠረተ ንግግር። መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ በማንበብ የሚገኙትን መንፈሳዊ ጥቅሞች ጎላ አድርገህ ግለጽ። የቀረቡትን ሐሳቦች ከልስና እንዴት በሥራ ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ግለጽ። ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች የአምላክን ቃል አዘውትረው በማንበባቸው የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 61 (144)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በኅዳር ወር ጥናት ያላስጀመሩ ካሉ በታኅሣሥም ወር ጥረታቸውን እንዲቀጥሉበት አበረታታ። በተጨማሪም “‘የአምላክ የሕይወት መንገድ’ ከተባለው የአውራጃ ስብሰባ ተጠቅመናል” ከሚለው ክፍል ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ።
10 ደቂቃ፦ የይሖዋ ምሥክሮችን የቀን መቁጠሪያ በሚገባ ተጠቀሙበት። በንግግር የሚቀርብ። የቀን መቁጠሪያውን ገጽታዎች ከልስ:- (1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጉልህ ክንውኖችንና ትምህርቶችን የሚያሳዩ ግሩም ሥዕሎች፣ (2) በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም የሚሸፈነው ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፣ (3) ከመታሰቢያው በዓል በፊት ባለው ሳምንት የሚነበበው ዓመታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም፣ (4) ቀጣዩ የክለሳ ጥያቄ የሚደረግበት ጊዜ፣ (5) መጽሔት በማበርከቱ አገልግሎት አዘውትረን እንድንካፈል የሚረዳ ማስታወሻ አካትቶ ይዟል። ክፍት የተተዉትን ቦታዎች የአገልግሎት ፕሮግራሞችን፣ የአገልግሎት ሪፖርቶችንና ከሌሎች ጋር ለማገልገል የምንይዛቸውን ቀጠሮዎች፣ የተሰጡንን ክፍሎች፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ የሚጎበኝበትንና የወረዳና የልዩ ስብሰባ ቀናት የሚደረጉበትን ጊዜ ለማስፈር ልንጠቀምባቸው እንችላለን። የቀን መቁጠሪያውን ቤታችን ወይም በሥራ ቦታ በቀላሉ ሊታይ በሚችል ቦታ ላይ ብናንጠለጥለው ቅዱስ ጽሑፋዊ ውይይት ለመጀመር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ሊከፍትልን ይችላል። በ1998 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ተሞክሮ ተናገር።
23 ደቂቃ፦ ሦስት ሽማግሌዎች የአውራጃ ስብሰባውን ፕሮግራም ይከልሳሉ። በስብሰባው ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር እያንዳንዳቸው የአንዱን ቀን ፕሮግራም ይሸፍናሉ።
መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።