የጥያቄ ሣጥን
◼ ክርስቲያኖች ለሕይወት ቅድስና ያላቸው አክብሮት በጊዜያችን የሚሠራባቸውን የቤተሰብ ምጣኔ ዘዴዎች በሚመለከት የትኞቹን ጉዳዮች በጥንቃቄ እንዲያመዛዝኑ ይገፋፋቸዋል?
ምንም እንኳ የቤተሰብ ምጣኔ የግል ውሳኔ ቢሆንም ክርስቲያኖች በማደግ ላይ ያለ ሕፃን እንዲጨነግፍ ወይም እንዲሞት የሚያደርግ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን አይጠቀሙም። መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት የሚጀምረው ሲጸነስ መሆኑን ይገልጻል። እንደ ዘጸአት 21:22, 23፣ ኤርምያስ 1:5 እና መዝሙር 139:16 የመሳሰሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አምላክ ያልተወለደው ሕፃን ሕይወት ውድ እንደሆነና መጥፋት እንደሌለበት አድርጎ እንደሚመለከት ያሳያሉ። ይህ ደግሞ የዳበረ እንቁላል በማሕፀን ግድግዳ ላይ እንዳይጣበቅ ሊከላከሉ በሚችሉ እንደ ሉፕ (IUD) በመባል የሚታወቀው በማሕፀን ውስጥ የሚቀመጥ መሣሪያና ፕሮጄስትሮን ብቻ ያለበትን እንክብል (ሚኒፒል፣ በክንድ ላይ እንደሚቀበረው ሆርሞን ያለ) በመሳሰሉት የእርግዝና መከላከያዎች መጠቀም የሚታሰብበት ጉዳይ ነው። በየካቲት 22, 1993 ንቁ! (አንግሊዝኛ) ገጽ 7-9 እና መጠበቂያ ግንብ 12-110 ገጽ 21 ላይ ተጨማሪ መረጃ ታትሞ ወጥቷል።