የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/99 ገጽ 8
  • “ምን ባደርግ ይሻላል?”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ምን ባደርግ ይሻላል?”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ዓይነት የሥራ መስክ መምረጥ ይሻለኛል?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
  • ወላጆች—ልጆቻችሁ ወደፊት ምን እንዲሆኑ ትፈልጋላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መከታተልን ጨርሶ አያበረታታምን?
    ንቁ!—1999
  • የትምህርት ቤት ሕይወታችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 4/99 ገጽ 8

“ምን ባደርግ ይሻላል?”

1 ሙሉ ሰው ወደ መሆን እየተቃረብህ ያለህ ወጣት ከሆንህ ‘በሕይወቴ ምን ባደርግ ይሻላል?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። ክርስቲያን ወጣቶች በስብከቱ ሥራ ለይሖዋ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ማሳደግ ይፈልጋሉ። ሆኖም በግል የሚያስፈልጉህን ቁሳዊ ነገሮች ማሟላትን ጨምሮ አንድ ጎልማሳ ሰው ያሉበትን ኃላፊነቶች ተሸክመህ ይህን መወጣት የምትችለው እንዴት ነው? የዚህን ጥያቄ መልስ ማግኘት ቀላል ላይሆን ይችላል።

2 አንዳንድ ወጣቶች የዓለምን የኢኮኖሚ ሁኔታና ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚሰነዘሩ ትንበያዎችን ሲመለከቱ ይጨነቃሉ ። ‘ተጨማሪ ዓለማዊ ትምህርት መከታተል ይኖርብኝ ይሆን? በቀጥታ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ብጀምር ይሻላል?’ እያሉ ያስባሉ። አንድ ሰው ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ‘በሕይወቴ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር ምንድን ነው?’ ለሚለው ጥያቄ ሐቀኝነት የተሞላበት መልስ መስጠት ይኖርበታል። የልቡን ሐሳብ መመርመር አለበት።

3 በወጣትነትህ ተቀዳሚ ዓላማ አድርገህ የያዝከው ነገር ምንድን ነው? ዋነኛው ፍላጎትህ ገንዘብ ነክ ጥቅሞች ማግኘት ነው? ወይስ በሕይወትህ ውስጥ በእርግጥ የመንግሥቱን ፍላጎቶች ማስቀደም ትፈልጋለህ? የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ መያዝ በሥራው ዓለም ስኬታማ ለመሆን ዋስትና አይሆንም። ብዙ ወጣቶች የሥራ ልምድ የሚያስገኙ ፕሮግራሞች፣ አንድ ዓይነት የተግባረ ዕድ ትምህርት ወይም ጥቂት ጊዜና ትኩረት ብቻ የሚሹ አጭር የኮሌጅ ትምህርቶችን አማራጭ አድርገው በመከታተል ተፈላጊ የሆኑ ሙያዎችን ማዳበር ችለዋል።

4 ይሖዋ በሰጠው ተስፋ ላይ እምነት ይኑርህ፦ ይሖዋ አምላክ በሕይወታቸው የመንግሥቱን ጥቅሞች በአንደኛ ደረጃ ለሚያስቀምጡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እንደሚያሟላላቸው የሰጠው ማረጋገጫ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ አስፈላጊ ነገር ነው። (ማቴ. 6:33) ይህ ከንቱ ተስፋ አይደለም። በአገልጋዮች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የተካፈሉ በርካታ ወንድሞች እውነትን ከመስማታቸው በፊት የኮሌጅ ዲግሪ ይዘው ነበር። ሆኖም የሚሠሩት ዓለማዊ ሥራ ምን ዓይነት ነው? ከተከታተሉት ትምህርት ጋር የሚጣጣም ሥራ የያዙት በጣም ጥቂቶች ናቸው። ብዙዎቹ አቅኚ ሆነው እያገለገሉም ወጪያቸውን በጥሩ ሁኔታ ሊሸፍን በሚችል የእጅ ሙያ ተሠማርተዋል። በአገልግሎት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማሳደግ ገንዘብ ሊያስገኝ ከሚችለው ከየትኛውም ነገር የሚበልጥ በረከት በማግኘት ላይ ናቸው።

5 ትምህርትህን ካጠናቀቅህ በኋላ ምን ማድረግ እንደምትፈልግ ለመወሰን ሁሉንም ነገሮች አመዛዝን፤ የልብህንም ሐሳብ በጥንቃቄ መርምር። በፊትህ የቀረቡትን ምርጫዎች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መመልከት እንድትችል በመጋቢት 1999 ንቁ! ገጽ 27-29 ላይ እንደወጣው ያሉ ርዕሶችን በጥሞና አንብብ። ወላጆችህን፣ ሽማግሌዎችን፣ የወረዳ የበላይ ተመልካችህን እንዲሁም በአካባቢህ የሚገኙ ስኬታማ የሆኑ አቅኚዎችን አነጋግር። እንዲህ ማድረግህ በሕይወትህ ምን ብታደርግ እንደሚሻል ጥበብ ያለበት ውሳኔ ላይ እንድትደርስ ይረዳሃል።—መክ. 12:1, 13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ