የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/99 ገጽ 5
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 12/99 ገጽ 5

የጥያቄ ሣጥን

◼ ለለቅሶ ሥነ ሥርዓት ተብሎ በአገር ልጅ ወይም በሠፈር ስም በተቋቋመ ማኅበር ውስጥ ስለ መሳተፍ ሊኖረን የሚገባው ትክክለኛ አመለካከት ምንድን ነው?

በብዙ አገሮች ውስጥ ሰዎች ለለቅሶ ሥነ ሥርዓት የሚያውሉትን ወጪ የሚሸፍን የኢንሹራንስ ዋስትና አላቸው። ሌሎች ደግሞ በመሥሪያ ቤታቸው ለተቋቋመ የመረዳጃ ማኅበር ገንዘብ ያዋጣሉ። በእኛ አገር ደግሞ እንደ እድር የመሳሰሉ በየአካባቢው የሚቋቋሙ ተመሳሳይ ማኅበሮች አሉ። ይሁን እንጂ አንድ ክርስቲያን የአንድ እድር አባል መሆን የሚያካትታቸውን የተለያዩ ገጽታዎች መመርመሩ አስፈላጊ ነው። እንዲህ ዓይነት ማኅበሮች የተመሠረቱባቸውን መመሪያዎች ወይም መተዳደሪያ ደንቦች እና የሚከተሏቸውን ልማዶች ስንመረምር አብዛኛውን ጊዜ ከቅዱስ ጽሑፋዊ እውነቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር ከሚጋጩ የጎሳ ወይም ሃይማኖታዊ ልማዶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን። (ያዕ. 1:27፤ ዮሐ. 17:16፤ ቆላ. 2:8) ምንም እንኳ እነዚህ ማኅበሮች በሆነ መንገድ አንዳቸው ከሌላው ሊለዩ ቢችሉም አብዛኞቹ በተለያየ እምነት በሚካሄዱ የለቅሶ ሥነ ሥርዓቶች መሳተፍን ይጠይቃሉ። ለምሳሌ ያህል አንዳንድ እድሮች ገንዘቡን የሚጠቀሙት ለሟቹ ተብሎ ለሚደረጉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ነው። “የምሥራቹ” አስፋፊ በመሆን ተቀባይነት ለማግኘት የሚፈልግ የእንዲህ ዓይነት ማኅበር አባል የሆነ ማንኛውም ሰው በ2 ቆሮንቶስ 6:14-17 እና በራእይ 18:4 ላይ የሚገኙትን ትእዛዛት ተግባራዊ ማድረግ ያለበት መሆኑን እንደሚገነዘብ የታወቀ ነው።

ለሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የገንዘብ ወጪ የማያደርግ እድር በሚኖርበት ጊዜም ጥበብ ባለበት መንገድ እየተመላለስን መሆናችንን ለማረጋገጥ ልንመረምራቸው የሚገቡ ሌሎች ነጥቦች አሉ። የእድር አባል መሆን በተሻለ መንገድ ጥቅም ላይ ልናውለው የምንችለውን ጊዜ ይሻማብናል። (ኤፌ. 5:15, 16) በተጨማሪም ከማያምኑ ሰዎች ጋር ኅብረት እንድንፈጥር ያደርገናል። ይህ ደግሞ መንፈሳዊነታችንን ሊያዳክምና ሕሊናችንን ሊያቆሽሽ ይችላል። (1 ጴጥ. 3:16፤ 1 ቆሮ. 15:33) የእድር ማኅበሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ከሞት ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች እንደሆነ ግልጽ ነው። በአንጻሩ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ከዚህ የተለየ አመለካከት እንድንይዝ ነው። ይህም በመሆኑ ጉባኤዎች የየራሳቸውን የለቅሶ ማኅበራት አያቋቁሙም። (ሉቃስ 9:60፤ 1 ተሰ. 4:13፤ ማቴ. 22:31, 32) እነዚህ ነጥቦች የእድርም ሆነ ተመሳሳይ የሆኑ ማኅበራት አባል መሆን ተገቢ እንዳልሆነ ያሳያሉ።

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ቀለል ያለና ሥርዓታማ የሆነ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቂ መሆኑን እንዲገነዘቡ መርዳት ያስፈልጋል። ለቀብር ተብለው የተቋቋሙ ማኅበራት አባል ሳይሆኑ በአገራችን ከሞቱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማኝ አምላኪዎች መካከል አንድም በወጉ ሳይቀበር የቀረ የለም። አንዳንድ ጊዜ ራሳቸው የቀብር ጉድጓዶችን ቆፍረው ወይም የሬሳ ሣጥኖችን ሠርተው አስፈላጊ የሆኑትን ዝግጅቶች በማድረግ ሳይቀር ወንድሞች እርስ በርስ ተደጋግፈዋል። (1 ጴጥ. 2:17) በጥሩ ሁኔታ በመደራጀት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የምግብና የትራንስፖርት ዝግጅቶችን ማስቀረት ተችሏል። አንዳንድ ቤተሰቦች በተገቢ መንገድ አስቀድመው በማሰብ ለእንዲህ ዓይነት ድንገተኛ አጋጣሚ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ ችለዋል። አንዳንዶች የግድ አስፈላጊ ያልሆነ አንድ የቤት ዕቃ በመሸጥ ወጪውን ሸፍነዋል። ለቀስተኛ ለመቀበል ዳስ ሳይተከል እንኳ ወንድማዊ ፍቅር በተግባር የታየባቸው አጋጣሚዎች የነበሩ ሲሆን አስፈላጊውን ማጽናኛ ለመስጠት ከማስቻላቸውም በላይ ጥሩ ምሥክርነት ሆነዋል።

አፍቃሪ የሆኑ ሽማግሌዎች በእንዲህ ዓይነት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝን ማንኛውንም ክርስቲያን ቤተሰብ ለመርዳት እንደሚጥሩ የተረጋገጠ ነው። በተለይ የቤተሰቡ አባላት ለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት የሚቸገሩ ከሆነ ይህ ነገር እውነት ነው። (ገላ. 6:9, 10) በተግባር ከሚደረግ እርዳታ በተጨማሪ ሽማግሌዎችና ሌሎች ወንድሞች አስፈላጊውን ማጽናኛም ይሰጣሉ። (1 ተሰ. 5:14) የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለው ብሮሹር በተለይ ደግሞ “ሌሎች እንዴት መርዳት ይችላሉ?” (ገጽ 20-24) በሚለው ርዕስ ሥር ስለዚህ ጉዳይ በጣም ተግባራዊ የሆነ ሐሳብ ቀርቧል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ አምላካዊ ጥበብና ይሖዋ የሚሰጠው እርዳታ ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል።—መዝ. 37:25፤ ማር. 10:28-30፤ ምሳሌ 3:3-6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ