ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርጉላቸውን ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ኮንትራት ማስገባት ይቻላል።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ሰብዓዊ አገዛዝ በሚዛን ሲመዘን” የሚል ይሆናል።
◼ ብዙ ወንድሞችና እህቶች የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ የግል ቅጂ እንደሌላቸው ማስተዋል ተችሏል። መጽሐፉ ሁላችንም የሚሰጡንን ክፍሎች በጥሩ ሁኔታ እንድንዘጋጅና ለክፍሉ ተማሪዎች የሚሰጠውን ምክር በመከታተል መጠቀም እንድንችል ይረዳናል። ይህ ግሩም መጽሐፍ በበቂ መጠን ስላለን ሁሉም ጉባኤዎች የሚያስፈልጋቸውን ያህል እንዲያዙ እናበረታታለን።
◼ ታላቅ ሰው የተባለው መጽሐፍ ተጠንቶ ካለቀ በኋላ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለው መጽሐፍ ይሆናል።