የ2001 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም መመሪያዎች
በ2001 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ትምህርቶቹ የተወሰዱባቸው ጽሑፎች፦ ክፍሎቹ በሚከተሉት ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ:- መጽሐፍ ቅዱስ [1954]፣ መጠበቂያ ግንብ [wAM]፣ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si ]፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው? [gtAM] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rsAM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ይከፈታል። በፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱትን ክፍሎች አስቀድሞ መናገር አስፈላጊ አይደለም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች እያንዳንዱን ክፍል ሲያስተዋውቅ ማብራሪያ የሚሰጥበትን ርዕስ ይናገራል። ክፍሎቹ በሚከተለው መንገድ ይከናወናሉ፦
ክፍል ቁ. 1፦ 15 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ሽማግሌ ወይም በአንድ የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ ወይም “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ በሚቀርብበት ጊዜ ለ15 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ሆኖ ይቀርባል። የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ” ከተባለው መጽሐፍ በሚቀርብበት ጊዜ ከ10 እስከ 12 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርብና በጽሑፉ ላይ ባሉት ጥያቄዎች በመጠቀም ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የክለሳ ጥያቄ ይቀርባል። ዓላማው የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለጉባኤው በጣም ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይገባል። በፕሮግራሙ ላይ የተጠቀሰውን ጭብጥ መጠቀም ይገባል።
ይህንን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች በተወሰነው ጊዜ ለመጨረስ ንቁ መሆን አለባቸው። አስፈላጊ ከሆነ ወይም ተናጋሪው ከጠየቀ በግል ምክር መስጠት ይቻላል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 6 ደቂቃ። ይህ ክፍል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በጥሩ ሁኔታ አዛምዶ ማቅረብ በሚችል ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ሊቀርብ ይገባል። ጭብጥ መስጠት አያስፈልግም። የተመደቡትን ምዕራፎች ሐሳብ በመከለስ ብቻ መቅረብ የለበትም። የተመደቡትን ምዕራፎች አጠቃላይ ሐሳብ ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ውስጥ መከለስ ይቻላል። ቢሆንም ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት ሊጠቅመን እንደሚችል እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ከዚህ በኋላ ተማሪዎቹ ወደየክፍላቸው መሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል አንድ ወንድም የሚያቀርበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ነው። ትምህርት ቤቱ በሚካሄድበት በዋናው አዳራሽም ይሁን በተጨማሪዎቹ ክፍሎች በዚሁ መንገድ ይቀርባል። ምንባቡ ብዙውን ጊዜ አጠር ያለ ስለሚሆን ተማሪው በመግቢያውና በመደምደሚያው ላይ መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት ያስችለዋል። ከበስተኋላ ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ትንቢታዊ ወይም መሠረተ ትምህርታዊ ትርጉሙንና የመሠረታዊ ሥርዓቶቹን ተግባራዊነት መጥቀስ ይቻላል። የተመደቡት ጥቅሶች በሙሉ ሳይቆራረጡ መነበብ ይኖርባቸዋል። የሚነበቡት ጥቅሶች ተከታታይ ካልሆኑ ግን ተማሪው ቀጥሎ የሚያነበውን ጥቅስ ቁጥር መናገር ይችላል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው እስከ ዛሬ ከኖሩት የሚበልጠው ታላቅ ሰው በተባለው መጽሐፍ ላይ ነው። መቼቱ መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት፣ ተመላልሶ መጠየቅ፣ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ሌላ ዓይነት የመስክ አገልግሎት ገጽታ ሊኖረው ይችላል። በክፍሉ ውስጥ የሚሳተፉ ክፍሉን ሲያቀርቡ መቀመጥ ወይም መቆም ይችላሉ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተለይ ተማሪዋ የቤቱን ባለቤት ስለ ትምህርቱ እንዲያስቡና ጥቅሶቹ እንዴት በሥራ ላይ እንደሚውሉ እንዲገነዘቡ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል፤ ሆኖም ተጨማሪ ረዳት ማዘጋጀት ይቻላል። በአንደኛ ደረጃ ሊታሰብበት የሚገባው መቼቱ ሳይሆን ትምህርቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ መቅረቡ ነው።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ላይ ነው። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም ወይም ለአንዲት እህት ይሰጣል። ክፍሉ ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ ለጠቅላላው ጉባኤ በንግግር መልክ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ ለእህት ከተሰጠ ለሦስተኛው ክፍል በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም፦ በጉባኤው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ግለሰብ በቀን አንድ ገጽ እንዲያነብ ሆኖ የተዘጋጀውን ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ተከትሎ እንዲያነብ ይበረታታል።
ማሳሰቢያ፦ ምክር መስጠትን፣ ጊዜ መጠበቅን፣ የክለሳ ጥያቄዎችና ክፍሎች መዘጋጀትን በሚመለከት ተጨማሪ ሐሳብ ወይም መመሪያ ለማግኘት የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3ን ተመልከቱ።
ፕሮግራም
ጥር 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 13–16
መዝሙር ቁ. 29 (62)
ቁ. 1፦ ይቅር ባይነት ለመዳን መንገድ ይከፍታል (w 99 1/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 14:1-14
ቁ. 3፦ በአምላክ ዘንድ የሚያስመሰግኑ ሥራዎችን መሥራት (gt ምዕ. 83)
ቁ. 4፦ ‘የራሴን ሰውነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመወሰን መብት አለኝ’ ለሚል ሰው መልስ መስጠት (rs ገጽ 26 አን. 5)
ጥር 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 17–20
መዝሙር ቁ. 66 (155)
ቁ. 1፦ ለመቀበል የማይከብድ ምክር (w 99 1/15 ገጽ 21–4)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 18:1–16
ቁ. 3፦ ደቀ መዝሙር መሆን የሚያስከትለው ኃላፊነት (gt ምዕ. 84)
ቁ. 4፦ ‘አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድና ዕቅድ ነበር’ ለሚል ሰው መልስ መስጠት (rs ገጽ 29 አን. 1–2)
ጥር 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 21–25
መዝሙር ቁ. 90 (204)
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 74 አን. 33–6)
ቁ 2፦ 2 ነገሥት 21:1–16
ቁ 3፦ ራሳችሁን ከማጽደቅ ተቆጠቡ፤ ትሕትናን ተከታተሉ (gt ምዕ. 85)
ቁ. 4፦ የቀድሞ አባቶችን ማምለክ ይሖዋ አምላክን የሚያሳዝነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 31 አን. 3-8)
ጥር 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 1–5
መዝሙር ቁ. 7 (19)
ቁ. 1፦ የ1 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 75–6 አን. 1–7)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 1:1–27
ቁ. 3፦ የጠፋው ልጅ እና አፍቃሪ አባቱ (gt ምዕ. 86 አን. 1–9)
ቁ. 4፦ ከሃዲዎችን ለይቶ ማወቅ (rs ገጽ 34-5 አን 2)
ጥር 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 6–10
መዝሙር ቁ. 58 (138)
ቁ. 1፦ እውነተኛ ትሕትና ማሳየት የሚቻልበት መንገድ (w 99 2/1 ገጽ 6–7)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 9:1–21
ቁ. 3፦ የጠፋው ልጅ መመለስ ሌሎችን ይነካል (gt ምዕ. 86 አን. 10–20)
ቁ. 4፦ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን በጴጥሮስ ላይ አልሠራም (rs ገጽ 36-8 አን. 4)
የካቲት 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 11–16
መዝሙር ቁ. 95 (213)
ቁ. 1፦ የማበረታቻ ምንጭ ሁኑ (w 99 2/15 ገጽ 26–9)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 11:1–19
ቁ. 3፦ በብልህነት የወደፊቱን ኑሮ ማመቻቸት (gt ምዕ. 87)
ቁ. 4፦ “የሐዋርያት ተተኪዎች” እውነተኛ ክርስቲያኖች አይደሉም (rs ገጽ 40 አን. 6-ገጽ 43 አን. 3)
የካቲት 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 17-23
መዝሙር ቁ. 79 (177)
ቁ. 1፦ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ (w 99 3/1 ገጽ 30–1)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 18:1–17
ቁ. 3፦ ሀብታሙ ሰውና አልዓዛር (gt ምዕ. 88 አን. 1–10)
ቁ. 4፦ አርማጌዶን ላይ የሚጠፋው ማን እና ምንድን ነው? (rs ገጽ 45 አን. 4-ገጽ 46 አን. 1)
የካቲት 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 24–29
መዝሙር ቁ. 87 (195)
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 78-9 አን. 22–5)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 29:1–13
ቁ. 3፦ የሀብታሙ ሰውና የአልዓዛር ምሳሌ ትርጉም ምንድን ነው? (gt ምዕ. 88 አን. 11–21)
ቁ. 4፦ አርማጌዶን—የአምላክን ፍቅር የሚጻረር አይደለም (rs ገጽ 46 አን. 8-ገጽ 47 አን. 2)
የካቲት 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 1–5
መዝሙር ቁ. 74 (168)
ቁ. 1፦ የ2 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 79–80 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 1:1–17
ቁ. 3፦ የምሕረት ተልዕኮ ለመፈጸም ወደ ይሁዳ መጓዝ (gt ምዕ. 89)
ቁ. 4፦ ብሔራትን ወደ አርማጌዶን እየነዳቸው ያለው የማን ግፊት ነው? (rs ገጽ 47 አን. 7–8)
መጋቢት 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 6–9
መዝሙር ቁ. 20 (45)
ቁ. 1፦ ራስህን ከልክ በላይ አታስጨንቅ (w 99 3/15 ገጽ 21–3)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 8:1–16
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ስለ ትንሣኤ ተስፋ ተናገረ (gt ምዕ. 90)
ቁ. 4፦ የጥንቷ ባቢሎን የታወቀችው በምኗ ነበር? (rs ገጽ 48 አን. 3-ገጽ 50 አን. 3)
መጋቢት 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 10–15
መዝሙር ቁ. 78 (175)
ቁ. 1፦ አስተሳሰብህን የሚቀርጸው ማን ነው? (w 99 4/1 ገጽ 20–2)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 10:1–16
ቁ. 3፦ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ (gt ምዕ. 91)
ቁ. 4፦ ከታላቂቱ ባቢሎን መውጣት በጣም አጣዳፊ የሆነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 51 አን. 4-ገጽ 52 አን. 3)
መጋቢት 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 16–20
መዝሙር ቁ. 48 (113)
ቁ. 1፦ በበኣል አምልኮ እንዳትማረክ ልብህን ጠብቅ (w 99 4/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 16:1–14
ቁ. 3፦ ለአምላክ ጥሩነት አመስጋኝ መሆን (gt ምዕ. 92)
ቁ. 4፦ የክርስቲያን የውኃ ጥምቀት የሚከናወነው ውኃ በመርጨት አይደለም፤ ሕፃናትም መጠመቅ አይኖርባቸውም (rs ገጽ 53 አን. 2–7)
መጋቢት 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 21–25
መዝሙር ቁ. 94 (212)
ቁ. 1፦ አድናቆትህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል (w 99 4/15 ገጽ 15–17)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 22:1–12
ቁ. 3፦ የሰው ልጅ ሲገለጥ (gt ምዕ. 93)
ቁ. 4፦ በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቁት እነማን ናቸው? (rs ገጽ 54 አን. 5-ገጽ 55 አን. 7)
ሚያዝያ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 26–29
መዝሙር ቁ. 24 (50)
ቁ. 1፦ አምላክ ‘በተጣመመ’ መንገድ ይሠራልን? (w 99 5/1 ገጽ 28–9)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 28:1–15
ቁ. 3፦ የጸሎትና የትሕትና አስፈላጊነት (gt ምዕ. 94)
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር የሚያደርጉን ምክንያቶች (rs ገጽ 57-58 አን. 4)
ሚያዝያ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 30-33
መዝሙር ቁ. 57 (136)
ቁ. 1፦ ሰዎች ይሖዋ አምላክን መባረክ የሚችሉት እንዴት ነው? (w 99 5/15 ገጽ 21-4)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 33:1-13
ቁ. 3፦ ስለ ፍቺና ልጆችን ስለ ማፍቀር የተሰጡ ትምህርቶች (gt ምዕ. 95)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ የተናገራቸው ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ማግኘታቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆኑን ያረጋግጣል (rs ገጽ 60 አን. 1–2)
ሚያዝያ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 34–36
መዝሙር ቁ. 61 (144)
ቁ. 1፦ 2 ዜና መዋዕል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 84 አን. 34–6)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 36:1–16
ቁ. 3፦ ኢየሱስና አንድ ሀብታም የሆነ ወጣት የሕዝብ አለቃ (gt ምዕ. 96)
ቁ. 4፦ aበመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሚሰነዘሩ የተቃውሞ ሐሳቦች መልስ መስጠት (rs ገጽ 63 አን. 1-ገጽ 67 አን. 1)
ሚያዝያ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 1–6
መዝሙር ቁ. 84 (190)
ቁ. 1፦ የዕዝራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
(si ገጽ 85 አን. 1-7፤ ገጽ 87 አን. 14-18)
ቁ. 2፦ ዕዝራ 4:1-16
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ስለ ወይን የአትክልት ቦታ የተናገረው ምሳሌ (gt ምዕ. 97)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ከደም መራቅ ያለባቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 69–71 አን. 1)
ሚያዝያ 30 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 7–10
መዝሙር ቁ. 4 (8)
ግንቦት 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 1–5
መዝሙር ቁ. 26 (56)
ቁ. 1፦ የነህምያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 88 አን. 1–5)
ቁ. 2፦ ነህምያ 1:1–11
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደፊት ለሚጠብቃቸው ነገር ከወዲሁ አዘጋጃቸው (gt ምዕ. 98)
ቁ. 4፦ *ስለ ደም ያለንን አቋም በተመለከተ ለሚሰነዘሩ የተቃውሞ ሐሳቦች መልስ መስጠት (rs ገጽ 73 አን. 1-ገጽ 75 አን. 1)
ግንቦት 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 6–9
መዝሙር ቁ. 66 (155)
ቁ. 1፦ ክርስቲያን ጉባኤ የብርታት ምንጭ ነው (w 99 5/15 ገጽ 25–8)
ቁ. 2፦ ነህምያ 9:1–15
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ጠፍቶ የነበረውን የአብርሃም ልጅ አገኘ (gt ምዕ. 99)
ቁ. 4፦ መዳን ‘እንደገና በመወለድ’ ላይ የተመካ አይደለም (rs ገጽ 76 አን. 7-ገጽ 77 አን. 5)
ግንቦት 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 10–13
መዝሙር ቁ. 21 (46)
ቁ. 1፦ ነህምያ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 90-1 አን. 16–19)
ቁ. 2፦ ነህምያ 12:27–43
ቁ. 3፦ የምናኑ ምሳሌ (gt ምዕ. 100)
ቁ. 4፦ ኃጢአትን ለቄስ መናዘዝ ወይም ማሳወቅ ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የለውም የሚባለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 79–80 አን. 8)
ግንቦት 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አስቴር 1–4
መዝሙር ቁ. 17 (38)
ቁ. 1፦ የአስቴር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 91–2 አን. 1–6)
ቁ. 2፦ አስቴር 1:1-15
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ማርያም ያደረገችውን መልካም ሥራ ደግፎ ተናገረ (gt ምዕ. 101)
ቁ. 4፦ ከባድ ኃጢአት በሚሠራበት ጊዜ ለሽማግሌዎች መናዘዝ የሚገባው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 82 አን. 7-ገጽ 83 አን. 2)
ሰኔ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አስቴር 5–10
መዝሙር ቁ. 16 (37)
ቁ. 1፦ የአስቴር መጽሐፍ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 94 አን. 16–18)
ቁ. 2፦ አስቴር 5:1–14
ቁ. 3፦ ክርስቶስ በድል ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (gt ምዕ. 102)
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት የሚዘግበውን ታሪክ መረዳት (rs ገጽ 85 አን. 4-ገጽ 87 አን. 2)
ሰኔ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 1–7
መዝሙር ቁ. 13 (33)
ቁ. 1፦ የኢዮብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 95-6 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 1:6-22
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የአምላክን ቤተ መቅደስ ያረከሱትን አወገዘ (gt ምዕ. 103)
ቁ. 4፦ ሰዎች ለምን ይሞታሉ? (rs ገጽ 97-99 አን. 1)
ሰኔ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 8–14
መዝሙር ቁ. 60 (143)
ቁ. 1፦ ሳውል—ለጌታ የተመረጠ ዕቃ (w 99 5/15 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 8:1–22
ቁ. 3፦ የአምላክ ድምፅ ለሦስተኛ ጊዜ ተሰማ (gt ምዕ. 104)
ቁ. 4፦ የይሖዋ ምሥክሮች በባሕላዊ የኀዘን ሥርዓት የማይካፈሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 102 አን. 1–7)
ሰኔ 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 15-21
መዝሙር ቁ. 36 (81)
ቁ. 1፦ አምላክ የሰጠውን ተስፋ በመፈጸም ረገድ አይዘገይም (w 99 6/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 17:1-16
ቁ. 3፦ የተረገመችው የበለስ ዛፍ ምንን ትወክላለች? (gt ምዕ. 105)
ቁ. 4፦ በመንፈስ አነሳሽነት የታዩና በመንፈስ አነሳሽነት ያልታዩ ሕልሞች (rs ገጽ 104–6 አን. 2)
ሐምሌ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 22–29
መዝሙር ቁ. 88 (200)
ቁ. 1፦ የአመለካከት አድማስህን ማስፋት ይኖርብህ ይሆን? (w 99 6/15 ገጽ 10–13)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 27:1–23
ቁ. 3፦ የሃይማኖት መሪዎች የተጋለጡት እንዴት ነበር? (gt ምዕ. 106)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ከማሪዋና መቆጠብ ያለባቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 108 አን. 3-ገጽ 109 አን. 3)
ሐምሌ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 30–35
መዝሙር ቁ. 80 (180)
ቁ. 1፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ማመን የምትችለው ለምንድን ነው? (w 99 7/15 ገጽ 4-8)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 31:1–22
ቁ. 3፦ የሠርጉ ድግስ ምሳሌ ትርጉም ምንድን ነው? (gt ምዕ. 107)
ቁ. 4፦ አንድን መጥፎ ልማድ ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 112 አን. 1–4)
ሐምሌ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 36–42
መዝሙር ቁ. 69 (160)
ቁ. 1፦ ኢዮብ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 100 አን. 39-43)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 36:1-22
ቁ. 3፦ ኢየሱስን ማጥመድ ሳይችሉ ቀሩ (gt ምዕ. 108)
ቁ. 4፦ ይሖዋ ምድርን በእሳት ያጠፋት ይሆን? (rs ገጽ 114 አን. 2-ገጽ 115 አን. 3)
ሐምሌ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 1–10
መዝሙር ቁ. 35 (79)
ቁ. 1፦ የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 1 (si ገጽ 101 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 3:1–4:8
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ተቃዋሚዎቹን አወገዘ (gt ምዕ. 109)
ቁ. 4፦ አምላክ ለምድር የነበረው የመጀመሪያ ዓላማው ተለውጧልን? (rs ገጽ 116 አን. 2-ገጽ 117 አን. 4)
ሐምሌ 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 11–18
መዝሙር ቁ. 23 (48)
ቁ. 1፦ የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 2 (si ገጽ 102 አን. 6-11)
ቁ. 2፦ መዝሙር 11:1-13:6
ቁ. 3፦ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ያከናወነው አገልግሎት ተፈጸመ (gt ምዕ. 110)
ቁ. 4፦ የሚወዷቸውን ዘመዶች በሞት ያጡ ሰዎችን ማጽናናት የምንችለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 118 አን. 5–9)
ነሐሴ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 19-26
መዝሙር ቁ. 9 (26)
ቁ. 1፦ ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ለተሳካ ትዳር ቁልፍ ነው (w 99 7/15 ገጽ 21–23)
ቁ. 2፦ መዝሙር 20:1–21:13
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የመጨረሻዎቹን ቀናት ምልክቶች ተናገረ (gt ምዕ. 111 አን. 1–11)
ቁ. 4፦ በፍትሕ መጓደል ምክንያት የሚተክዙ ሰዎችን ማጽናናት የምትችለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 119 አን. 7-ገጽ 120 አን. 2)
ነሐሴ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 27–34
መዝሙር ቁ. 53 (130)
ቁ. 1፦ ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ (w 99 7/15 ገጽ 24-5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 28:1-29:11
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት ተጨማሪ ምልክቶችን ተናገረ (gt ምዕ. 111 አን. 12-19)
ቁ. 4፦ በጉድለቶታቸው ምክንያት ቅስማቸው የተሰበረባቸውን ሰዎች ማጽናናት (rs ገጽ 120 አን. 8-ገጽ 121 አን. 2)
ነሐሴ 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 35–39
መዝሙር ቁ. 51 (127)
ቁ. 1፦ እኩዮች ከሚያሳድሩት ተጽዕኖ ጥቅም ማግኘት ይቻል ይሆን? (w 99 8/1 ገጽ 22-5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 38:1–22
ቁ. 3፦ ልባሞቹና ሰነፎቹ ቆነጃጅት (gt ምዕ. 111 አን. 20–8)
ቁ. 4፦ ዝግመተ ለውጥ፣ የቅሪተ አካል መረጃና ምክንያታዊነት (rs ገጽ 123 አን. 3-ገጽ 126 አን. 5)
ነሐሴ 27 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 40–47
መዝሙር ቁ. 34 (77)
መስከረም 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 48-55
መዝሙር ቁ. 71 (163)
ቁ. 1፦ ቁጣ እንዳያሰናክልህ ተጠንቀቅ (w 99 8/15 ገጽ 8–9)
ቁ. 2፦ መዝሙር 49:1–20
ቁ. 3፦ የመክሊቱ ምሳሌ (gt ምዕ. 111 አን. 29–37)
ቁ. 4፦ ብዙ ሰዎች እምነት የሌላቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 130-131 አን. 2)
መስከረም 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 56-65
መዝሙር ቁ. 56 (135)
ቁ. 1፦ እንድንታመም የሚያደርገን ዲያብሎስ ነውን? (w 99 9/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ መዝሙር 59:1–17
ቁ. 3፦ ክርስቶስ በመንግሥቱ ሥልጣን በሚመጣበት ጊዜ (gt ምዕ. 111 አን. 38–46)
ቁ. 4፦ ጽድቅ የሚኖርበት አዲስ ሥርዓት እንደሚመጣ ማመናችንን በሥራ ማሳየት (rs ገጽ 132 አን. 3-ገጽ 133 አን. 1)
መስከረም 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 66–71
መዝሙር ቁ. 31 (67)
ቁ. 1፦ “የሚሻለውን” ምረጥ (w 99 9/1 ገጽ 30–1)
ቁ. 2፦ መዝሙር 69:1–19
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ (gt ምዕ. 112)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መቼና እንዴት እንደሚፈጸም የሚያውቁት ሁልጊዜ አልነበረም (rs ገጽ 135 አን. 1–6)
መስከረም 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 72-77
መዝሙር ቁ. 97 (217)
ቁ. 1፦ ቃልህን መጠበቅ የሚኖርብህ ለምንድን ነው? (w 99 9/15 ገጽ 8–11)
ቁ. 2፦ መዝሙር 73:1–24
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ስለ ትሕትና አስተማረ (gt ምዕ. 113)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ነቢያት በፍሬያቸው ተለይተው ይታወቃሉ (rs ገጽ 136 አን. 1-ገጽ 137 አን. 2)
ጥቅምት 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 78–81
መዝሙር ቁ. 22 (47)
ቁ. 1፦ ጥበብን አግኝ ተግሣጽንም ተቀበል (w 99 9/15 ገጽ 12–15)
ቁ. 2፦ መዝሙር 78:1-22
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የመታሰቢያውን በዓል አቋቋመ (gt ምዕ. 114)
ቁ. 4፦ አምላክ እያንዳንዱ ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አስቀድሞ አልወሰነም (rs ገጽ 138-139 አን. 1)
ጥቅምት 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 82-89
መዝሙር ቁ. 99 (221)
ቁ. 1፦ ጢሞቴዎስ ‘በእምነት እውነተኛ ልጅ የሆነ’ (w 99 9/15 ገጽ 29–31)
ቁ. 2፦ መዝሙር 88:1–18
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ፍቅርንና ትሕትናን በትዕግሥት አስተማራቸው (gt ምዕ. 115)
ቁ. 4፦ አምላክ እያንዳንዱን ነገር በቅድሚያ አያውቅም እንዲሁም አይወስንም (rs ገጽ 140 አን. 8-ገጽ 141 አን. 2)
ጥቅምት 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 90–98
መዝሙር ቁ. 77 (174)
ቁ. 1፦ መጥፎ ድርጊትን እምቢ ለማለት የሚያስችል ጥንካሬ ማግኘት (w 99 10/1 ገጽ 28–31)
ቁ. 2፦ መዝሙር 90:1–17
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ሐዋርያቱን ከእነርሱ ለሚለይበት ጊዜ አዘጋጃቸው (gt ምዕ. 116 አን. 1–14)
ቁ. 4፦ አምላክ አዳም ኃጢአት እንደሚሠራ ለማወቅ አስቀድሞ የማወቅ ችሎታውን ለምን አልተጠቀመም? (rs ገጽ 142 አን. 3-ገጽ 143 አን. 1)
ጥቅምት 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 99–105
መዝሙር ቁ. 41 (89)
ቁ. 1፦ የላቀውን የፍቅር መንገድ መማር (w 99 10/15 ገጽ 8-11)
ቁ. 2፦ መዝሙር 103:1-22
ቁ. 3፦ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጆች እነማን ናቸው? (gt ምዕ. 116 አን. 15-25)
ቁ. 4፦ የክርስቲያን ጉባኤ የወደፊት ሁኔታ አስቀድሞ የተወሰነው በምን መንገድ ነው? (rs ገጽ 144 አን.2-3)
ጥቅምት 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 106-109
መዝሙር ቁ. 45 (106)
ቁ. 1፦ “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል” (w 99 11/15 ገጽ 24–7)
ቁ. 2፦ መዝሙር 107:1–19
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አዘጋጃቸው እንዲሁም አበረታታቸው (gt ምዕ. 116 አን. 26–37)
ቁ. 4፦ በአምላክ ለማመን የሚያበቁ ጥሩ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው? (rs ገጽ 146-47 አን. 2)
ኅዳር 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 110–118
መዝሙር ቁ. 33 (72)
ቁ. 1፦ አፖካሊፕስ—የሚያስፈራ ወይስ በተስፋ የሚጠበቅ? (w 99 12/1 ገጽ 5–8)
ቁ. 2፦ መዝሙር 112:1–113:9
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ደርብ ላይ በሚገኝ ክፍል ያደረገው የመደምደሚያ ጸሎት (gt ምዕ. 116 አን. 38–51)
ቁ. 4፦ አምላክ ስሜት ያለው የተወሰነ አካል ነው (rs ገጽ 148 አን. 1–7)
ኅዳር 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 119
መዝሙር ቁ. 15 (35)
ቁ. 1፦ ጠንካራ ጎናችሁ ለድክመት ምክንያት እንዲሆን አትፍቀዱ (w 99 12/1 ገጽ 26–9)
ቁ. 2፦ መዝሙር 119:1–24
ቁ. 3፦ በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ (gt ምዕ. 117)
ቁ. 4፦ በአምላክ ስም መጠቀም ለመዳን አስፈላጊ ነው (rs ገጽ 149 አን. 3-ገጽ 150 አን. 1)
ኅዳር 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 120–137
መዝሙር ቁ. 78 (175)
ቁ. 1፦ መዝሙር ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 1 (si ገጽ 104–5 አን. 23–7)
ቁ. 2፦ መዝሙር 120:1–122:9
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የተፈጸመበት ክህደት እና መያዙ (gt ምዕ. 118)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ምን ዓይነት “አምላክ” ነው? (rs ገጽ 150 አን. 6–7)
ኅዳር 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 138–150
መዝሙር ቁ. 56 (135)
ቁ. 1፦ መዝሙር ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 2 (si ገጽ 105–6 አን. 28–32)
ቁ. 2፦ መዝሙር 139:1–24
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ያለአግባብ ተሰደበ እንዲሁም ፍርድ ቤት ቀረበ (gt ምዕ. 119)
ቁ. 4፦ ሰዎች ፍትሐዊ መስተዳድር መመሥረት የማይችሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 153 አን. 1–6)
ታኅሣሥ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 1–7
ዝሙር ቁ. 54 (132)
ቁ. 1፦ የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 1 (si ገጽ 106–7 አን. 1–5)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 4:1–27
ቁ. 3፦ ጴጥሮስ ኢየሱስን እንዲክድ ያደረገው የሰው ፍርሃት ነው (gt ምዕ. 120)
ቁ. 4፦ የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት የሚሟላው በአምላክ መንግሥት ብቻ ነው (rs ገጽ 155 አን. 1–ገጽ 156 አን. 1)
ታኅሣሥ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 8–13
መዝሙር ቁ. 85 (191)
ቁ. 1፦ የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 2 (si ገጽ 107–8 አን. 6–11)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 13:1–25
ቁ. 3፦ ኢየሱስ በሳንሄድሪንና በጲላጦስ ፊት በቀረበ ጊዜ በድፍረት እውነት ተናገረ (gt ምዕ. 121)
ቁ. 4፦ በዘመናችን በአምላክ መንፈስ እርዳታ ተአምራዊ ፈውስ አይደረግም (rs ገጽ 157-158 አን. 2)
ታኅሣሥ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 14–19
መዝሙር ቁ. 30 (63)
ቁ. 1፦ ምሳሌ ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 1 (si ገጽ 109–10 አን. 19–28)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 16:1–25
ቁ. 3፦ ጲላጦስም ሆነ ሄሮድስ በኢየሱስ ላይ አንዳች ጥፋት ሊያገኙበት አልቻሉም (gt ምዕ. 122)
ቁ. 4፦ በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁበት መንገድ (rs ገጽ 159 አን. 1–5)
ታኅሣሥ 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 20–25
መዝሙር ቁ. 93 (211)
ቁ. 1፦ ምሳሌ ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 2 (si ገጽ 110–11 አን. 29–38)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 20:1–30
ቁ. 3፦ ኢየሱስ “ሰውዬው” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት (gt ምዕ. 123)
ቁ. 4፦ መላው የሰው ዘር እውነተኛ ፈውስ እንዲያገኝ ምን ተስፋ አለ? (rs ገጽ 161 አን. 2–4)
ታኅሣሥ 31 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 26-31
መዝሙር ቁ. 80 (180)
[የግርጌ ማስታወሻ]
a የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።