የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/00 ገጽ 9
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 10/00 ገጽ 9

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርጉላቸው ሰዎች ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ከጥቅምት 16 ጀምሮ የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ማሰራጨት ይጀመራል። ኅዳር:- የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ስርጭት ይቀጥላል። ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ የቤት ባለቤት የመንግሥት ዜና ቁጥር 36ን አበርክተው ከጨረሱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ለዘላለም መኖር ወይም ፍጥረት የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉት መጻሕፍት። ጥር:- ከ1986 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የሚለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ።

◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ ያለው አባሪ “የ2001 ቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።

◼ የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ከጥር 1 ጀምሮ የሚቀየር ከሆነ ጸሐፊው የጉባኤ ስብሰባዎች መረጃ (S-5) እና የጥሪ ወረቀት ማዘዣ የሚሉትን ቅጾች (S-16) በመላክ ለውጡን ለማኅበሩ ማሳወቅ ይገባዋል። አስፈላጊ ከሆነ በዚያው ቅጽ ተጠቅሞ አዲስ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ ይቻላል። መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ የሚገባችሁ እንዲደርሳችሁ ከምትፈልጉበት ጊዜ ቢያንስ ከስምንት ሳምንታት በፊት መሆን አለበት።

◼ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችሁን ስትመልሱ ሪፖርቱ ማካተት ያለበት ከወሩ የመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከዚያ ወር የመጨረሻ ቀን ድረስ በመስክ አገልግሎት ያሳለፋችሁትን እንቅስቃሴ ብቻ መሆን እንዳለበት ልናስታውሳችሁ እንወዳለን። ሪፖርት የምትመልሱት ወሩ ካለቀ ከጥቂት ቀናት በኋላም ይሁን በፊት የመስክ አገልግሎት ሰዓታችሁን ከአንዱ ወር ወደ ሌላው ማሸጋገር አይኖርባችሁም። ለምሳሌ ያህል የወሩ የመጨረሻ ቀን ሐሙስ ቢሆንና ሪፖርት የምትመልሱት ደግሞ በቀጣዩ እሁድ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ቢሆን ዓርብና ቅዳሜ የምታገለግሉትን በሪፖርቱ ማካተት አይኖርባችሁም። ከዚህ ይልቅ በሁለቱ ቀናት ያሳለፋችሁትን የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመለስ የሚገባችሁ በቀጣዩ ወር ነው። ይህ መመሪያ ለአስፋፊዎችም ሆነ ለአቅኚዎች ይሠራል። መጠኑ አነስተኛም ቢሆን ወይም በወቅቱ ከአካባቢው ርቃችሁ ብትኖሩም በእያንዳንዱ ወር ሪፖርታችሁን በሰዓቱ እንድትመልሱ እናበረታታችኋለን።

◼ ጉባኤዎች ከጥቅምት ወር የጽሑፍ ጥያቄያቸው ጋር ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2001ን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል።

◼ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን አማርኛ ብሮሹር ማዘዝ ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ