የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ሚያዝያ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 69 (160)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የጉባኤው የመታሰቢያ በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር ስንት እንደነበር ተናገር። በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙ ሰዎች በአድናቆት የሰጡት አስተያየት ካለ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ሁሉም ሚያዝያ 23 በሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ—በሕይወትህ ውስጥ ያለው ኃይል ስለተባለው ቪዲዮ በውይይት ለሚቀርበው ክፍል ለመዘጋጀት አስቀድመው ፊልሙን አይተው እንዲመጡ አበረታታ።
10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የመጽሐፍ ጥናት የሚደረግበትን ቤት በመምረጥ ረገድ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነገሮችን ጨምረህ አቅርብ።—የካቲት 1983 የመንግሥት አገልግሎታችን (እንግሊዝኛ) ላይ የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- “በአገልግሎታችሁ ‘ትጉ’።”* ከአንቀጽ 3-5 ላይ በተሰጠው ሐሳብ መሠረት ሌሎችን በመርዳት ረገድ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎችን ጋብዝ።
መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 16 የሚጀምር ሳምንት።
መዝሙር 29 (62)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ሚያዝያ ሊገባደድ ሁለት ሳምንታት ብቻ ስለቀሩት ከዚያ ፊት ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- “ቀላል አቀራረብ ከሁሉ የተሻለ ነው።”* ከሐምሌ 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 “‘ፍሬ ነገሩን’ እንናገር!” ከሚለው ርዕስ ላይ ተጨማሪ ሐሳቦች አቅርብ። አንድ ወይም ሁለት ቀላል አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “አስቀድሞ እቅድ ማውጣት—ምን ለማድረግ?” በንግግር የሚቀርብ። ከኅዳር 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-21 ላይ ተስማሚ ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ።
25 ደቂቃ:- “መጽሐፍ ቅዱስ —በሕይወትህ ውስጥ ያለው ኃይል የተባለው ቪዲዮ የነካችሁ እንዴት ነው?” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። የማኅበሩን የቪዲዮ ክሮች በጥሩ ሁኔታ መጠቀምን በተመለከተ በ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 54 አንቀጽ 1 ላይ በተጠቀሰው ተሞክሮ ውስጥ የተሰጠውን ሐሳብ ለምን አትሠሩበትም? በሰኔ ወር የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተቋቁመዋል የተባለውን የቪዲዮ ክር እንከልሳለን።
መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 96 (215)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሚያዝያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። የጉባኤውን ሪፖርት እስከ ግንቦት 6 ማጠናቀር እንዲቻል የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አስፋፊ ሪፖርት መመለሱን መከታተል አለባቸው።
15 ደቂቃ:- “ጥሩ ጎረቤት በመሆን ምሥክርነቱን ስጡ።”* በጠባያችን ምሥክርነት መስጠት የምንችልባቸውን ተጨማሪ መንገዶች ጥቀስ።—የኅዳር 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18 አንቀጽ 16ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- አቅኚዎች ሌሎችን እየረዱ ነው። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና በቃለ ምልልስ ያቀርበዋል። በመስከረም 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን አቅኚዎች ሌሎችን የሚረዱበትን ፕሮግራም ከልስ። ጉባኤው በዚህ ረገድ ስላገኛቸው ገንቢ ውጤቶች ተናገር። ሌላ አስፋፊ ከረዳ/ች አቅኚ እና በአቅኚ ከተረዳ/ች አስፋፊ ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ሁለቱም አንድ ላይ በማገልገላቸው ያገኙትን ጥቅም ተናገር። በሚቀጥሉት ወራት ሌሎችም በዚህ ዝግጅት እንዲጠቀሙ ጋብዝ።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ‘በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል።’* በ1935 ስብከቱ ምን ያህል እንደተከናወነ ለማሳየት አዋጅ ነጋሪዎች በተባለው መጽሐፍ ገጽ 443 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ መጨረሻ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ አኃዛዊ መረጃ ጋር በማወዳደር በአጭሩ ሐሳብ ስጥ። ይህ አስደናቂ እድገት በአንድ ወቅት እንዴት የማይቻል ይመስል እንደነበር ተናገር።
20 ደቂቃ:- ቤተሰባችን ቅድስናን ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው? አንድ ሽማግሌ ከቤተሰቡ ጋር በነሐሴ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-20 ላይ ውይይት ያደርጋል። በቤት፣ ከዘመዶች ጋር፣ በጉባኤ ውስጥ እና በጎረቤቶቻችን አካባቢ እንዲሁም በትምህርት ቤትና በሥራ ቦታ ቅድስናን ማሳየት የምንችልባቸውን መንገዶች ተናገር።
መዝሙር 32 (70) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
*ከአንድ ደቂቃ በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት አቅርበው።