የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ግንቦት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 (3)
6 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች እና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
25 ደቂቃ:- ሕክምናን በተመለከተ የተደረጉልን ፍቅራዊ ዝግጅቶች። ማኅበሩ በላከው አስተዋጽኦ ላይ የተመሠረተ ጥሩ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ከፍላጎታችን ውጪ ደም እንዳይሰጠን መከላከል የሚቻልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ እና ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የሚሉትን ሁለት ሰነዶች መሙላት እንደሆነ ጠበቅ አድርገህ ተናገር። የተጠመቁ አስፋፊዎች ዛሬ ምሽት ስብሰባው ካለቀ በኋላ እነዚህን ሰነዶች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የሚሞላው ግን ዛሬ አይደለም። ሦስቱንም ሰነዶች ማለትም ካርዱን፣ ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የሚለውንና የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያውን ማሰራጨት እንዲቻል ጉባኤው እነዚህ ሰነዶች በበቂ መጠን ሊኖሩት ይገባል። የሰነዱ ባለቤትም ሆነ ምሥክሮቹ በሰነዶቹ ላይ የሚፈርሙትና ቀን የሚሞላባቸው ከፊታችን የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ አስፈላጊ ሲሆንም በመጽሐፍ ጥናቱ መሪ እርዳታ ይሆናል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙ ሰዎች የሰነዱ ባለቤት ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። ሁለቱ ሰነዶች ሙሉ በሙሉ ከመሞላታቸው በፊት ማኅበሩ ያዘጋጀው የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ በጥንቃቄ መነበብ ይኖርበታል። የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያሉት አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠውን የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ እና ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የሚሉትን ሰነዶች መሙላት እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማግኘታቸውን መከታተል አለባቸው። ወላጆች ከዚህ ስብሰባ በኋላ ለልጆቻቸው የመታወቂያ ካርድ ሊወስዱላቸው ይችላሉ። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከእነዚህ ሰነዶች ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው መመሪያ ማዘጋጀት ይችላሉ።
14 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። እባክህ ይህን ክፍል በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያላቸውን ሥርዓቶች ሁሉ ማስወገድ እንደምንፈልግ ጎላ አድርገህ ተናገር። በእምነት አጋሮቻችን መካከል ጸሎትና የተለመደው የመልካም ምኞት መግለጫ በቂ ነው። ከዚያ ውጪ እንደ አንድ ዓይነት ሥርዓት ተቆጥረው የሚከናወኑ ምርቃቶች አስፈላጊ አይደሉም። የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ዘመዶች ካልመረቅን የሚሉ ከሆነ ሙሽራው አስቀድሞ በዚህ ረገድ ያለውን አመለካከት የመግለጽና ምርቃት የሚፈልግም ከሆነ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት አስቀድሞ የማወቅ ኃላፊነት ይኖርበታል።
መዝሙር 79 (177) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 (112)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
17 ደቂቃ:- “የአገልግሎት ክልላችንን ደጋግመን ሸፍነናል!” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። (የአገልግሎት ክልላቸውን በተደጋጋሚ ያልሸፈኑ ጉባኤዎች ከሚያዝያ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “መጽሔቶች መንግሥቱን ያስታውቃሉ” የሚለውን ርዕስ ማቅረብ ይችላሉ።) በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ ስትሠሩ ክልሉን ይበልጥ አጣርታችሁ ለመሸፈን ምን ማድረግ እንደሚቻል ተወያዩ። በ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 204 ላይ እና በየካቲት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 26 ላይ የሚገኙ ተሞክሮዎችን ተናገር። በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ ከቤት ወደ ቤት መመዝገቢያ ማዘጋጀት፣ ቤታቸው ያልተገኙትን ሰዎች ተከታትሎ መርዳትና ተመላልሶ መጠየቆችን በቶሎ ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
18 ደቂቃ:- አንድ ሽማግሌ ከየካቲት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ላይ “በመጽናት የሚገኝ ስኬት” የሚለውን ርዕስ በንግግር ያቀርብና በክለሳ ጥያቄዎች ይደመድማል።
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎችን ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
17 ደቂቃ:- ‘የአምላክ ቃል ይሠራል።’ ከአንድ ደቂቃ በሚያንስ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አጫጭር አቀራረቦችን በመጠቀም ሰዎችን እንዴት ወደ አምላክ ቃል መሳብ እንደሚቻል ለማሳየት ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 (33)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመስክ አገልግሎት የተገኙ ተሞክሮዎች።
15 ደቂቃ:- “በመከሩ ሥራ በሙሉ አቅማችሁ ተካፈሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 4 ላይ ውይይት ስታደርጉ አንዳንዶች አገልግሎታቸውን ለማስፋት ምን እንዳደረጉ ለማሳየት በመስከረም 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18 አንቀጽ 10 ላይ የሚገኘውን ምሳሌ ጥቀስ።
18 ደቂቃ:- ግሩም ሆነው የተዘጋጁትን የማስተማሪያ መሣሪያዎቻችንን በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ የማስጠናት እንቅስቃሴያችንን ማሻሻል። (ከሰኔ 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚቀርብ) እያንዳንዱን አንቀጽ በማንበብ ተወያዩበት። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የእውቀት መጽሐፍ ገጽ 83 ላይ ሲደርስ ክፉ ሰዎች የሚቀጡበት ዘላለማዊ የቅጣት ቦታ አለ ብሎ ሲከራከር የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ከዚያም የጥናቱ መሪ ለዘላለም መኖር ምዕራፍ 8ን እንዲያነብ ይጋብዘውና በቀጣዩ ሳምንት በዚሁ ምዕራፍ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ እንደሚወያዩ ይነግረዋል።
መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።