የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 8/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

ነሐሴ 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

13 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ነሐሴ 27 በሚጀምር ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በእንቅስቃሴ ላይ በተባለው ቪዲዮ ላይ ውይይት ስለሚደረግ ሁሉም አስቀድመው ፊልሙን በማየት እንዲዘጋጁ አበረታታ።

17 ደቂቃ:- “የበለጠ መሥራት ትፈልጋላችሁ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

15 ደቂቃ:- “ለመዝናኛ ገደብ አብጁ።” አንድ የመጽሐፍ ጥናት መሪ ከመጽሐፍ ጥናት በኋላ ከአንድ ባልና ሚስት ጋር ይወያያል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመስክ አገልግሎት ላይ ወይም በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በሚደረጉት የጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንደማያያቸው በደግነት ይነግራቸዋል። ባልና ሚስቱ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ጊዜ እንዳሳጧቸው ይናገራሉ። ሽማግሌው በርዕሰ ትምህርቱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ነጥቦች በመከለስ መንፈሳዊ ጉዳዮች ምንጊዜም የመጀመሪያውን ቦታ መያዝ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል። ባልና ሚስቱ ስለ መልካም ማሳሰቢያው አመስጋኝነታቸውን ይገልጻሉ። ለወደፊቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለማስቀደም ይስማማሉ።​—⁠የጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-20ን ተመልከት።

መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13 (33)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- “‘በመድረክ ላይ እንዳለ ተዋናይ’ ናችሁ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች ስለሚያከናውኑት ሥራ ወይም ስለሚያሳዩት ጠባይ ከሰጡት ገንቢ አስተያየት መካከል ጥቂት ምሳሌዎች ጥቀስ።​—⁠የመጋቢት 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10ን እና የጥር 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32ን ተመልከት።

22 ደቂቃ:- “ሥርዓታማነት​—⁠ለአምላክ ያደሩ ሰዎች መለያ።” አንድ ሽማግሌ ከአንቀጽ 1-5 ላይ የተመሠረተ የአምስት ደቂቃ ንግግር ያቀርባል። ከዚያም ቀሪውን ክፍል ከሌላ ሽማግሌና የጉባኤ አገልጋይ ጋር ይወያይበታል። በስብሰባዎቻችን ላይ ትኩረታችንን ሊሰርቁና ማግኘት የሚገባንን ጥቅም ሊቀንሱ የሚችሉ አሳቢነት የጎደላቸውን ልማዶች እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ይነጋገራሉ። ለሌሎች ጥቅም ፍቅራዊ አሳቢነት ስናሳይ አብረን የምናሳልፈው ጊዜ ምን ያህል አበረታች እንደሚሆን ጎላ አድርገው ይገልጻሉ።​—⁠ፊልጵ. 2:​4

መዝሙር 33 (72) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 54 (132)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውስ። በመስከረም ወር ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ በአገልግሎት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚጠቁሙ አንድ ወይም ሁለት ሐሳቦችን በአጭሩ ተናገር።​—⁠በመስከረም 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 እና በመስከረም 1995 ገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ምሳሌዎች ተመልከት።

22 ደቂቃ:- “‘በማዳመጥ ተጨማሪ ትምህርት ቅሰሙ።’” የቤተሰብ ውይይት። በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የሚቀርበው ትምህርት በጣም የሚያስፈልገን መንፈሳዊ ምግብ የሆነው ለምን እንደሆነ ግለጽ። እንዲህ ዓይነቱን ፕሮግራም ለማዘጋጀት የሚባክነውን ጊዜና ጉልበት አስመልክተህ ሐሳብ ስጥ። እያንዳንዱ ሰው ራሱም ሆነ ሌሎች ከፍተኛ ጥቅም እንዲያገኙ ምን ማድረግ እንደሚችል ሐሳብ ስጥ። ሁላችንም እያንዳንዱ የስብሰባው ክፍለ ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ቦታችን ላይ መገኘት ያለብን ለምን እንደሆነ ጠበቅ አድርገህ ተናገር።

15 ደቂቃ:- “የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በእንቅስቃሴ ላይ የተባለው ፊልም ታሪካዊ ቅኝት።” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይትና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። በጥቅምት ወር በመለኮታዊ ትምህርት አንድ መሆን የተባለውን ቪዲዮ እንከልሳለን።

መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 51 (127)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ:- “ክርስቲያናዊ ወዳጅነት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከጥር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22 ላይ “በጉባኤ አማካኝነት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን አንዳንድ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ። በውይይትና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸው ሰዎች ያልጠበቅነውን ሐሳብ ሲሰነዝሩ ወይም ጥያቄዎች ሲጠይቁ ርዕስ ለመቀየር ከመሞከር ወይም ውይይቱን ከማስቆም ይልቅ መልስ ለመስጠት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ ረገድ ማመራመር የተባለው መጽሐፍ ሊረዳን ይችላል። አንዳንድ የተለመዱ አስተያየቶችን ጥቀስና አስፋፊዎች በማመራመር መጽሐፍ ላይ በተጠቀሰው ሐሳብ መሠረት እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ያቅርቡ። ለምሳሌ ያህል:- ‘በአምላክ አላምንም።’ (ገጽ 151-2) ‘እናንተ የኅብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ለምን አትካፈሉም?’ (ገጽ 208-9) ‘የየትኛውም ቤተ ክርስቲያን አባል ብትሆን ለውጥ የለውም።’ (ገጽ 331) ሁሉም በአገልግሎት ላይ ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ሲያጋጥሟቸው ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ‘አንድ ሰው እንዲህ ቢልህስ’ የሚለውን ክፍል እንዲጠቀሙ አበረታታ።

መዝሙር 46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ