ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች በኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ሌላ የቆየ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ እና ጥር:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ፣ “መንግሥትህ ትምጣ” የተባለውን መጽሐፍም ማበርከት ይቻላል። የካቲት:- ራእይ ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም ጉባኤው ያለውን ማንኛውንም የቆየ ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነገር አለበት።
◼ በዚህ ዓመት በሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ክልል የመሸፈን ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ውስጥ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች በትልቅ ሉክ ወረቀት ጽፈው እስከ ታኅሣሥ 31, 2001 ድረስ ሊልኩልን ይገባል:- 1) ስም 2) ዕድሜ 3) የተጠመቁበት ቀን 4) የጋብቻ ሁኔታ [ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት] 5) ለማገልገል የምትችልባቸው ወራት [ከመጋቢት እስከ ግንቦት?] 6) የምትናገራቸው ቋንቋዎች 7) አመልካቹ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ አዘውትሮ የሚካፈል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ድጋፍና ፊርማ ያክሉበታል።
◼ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለው መጽሐፍ ከታኅሣሥ 10, 2001 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22, 2002 ድረስ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ ይጠናል። የጥናቱን ፕሮግራም በታኅሣሥ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
◼ አዲስ የደረሱን፦ እንግሊዝኛ:- T-71፤ ዳዝ ፌት ሩል ዩር ላይፍ?፤ T-72 ዘ ግሬተስት ኔም (ለሙስሊሞች)፤ T-73 ሁ አር ጀሆቫስ ዊትነስስ?፤ T-74 ሄል ፋየር—ኢዝ ኢት ፓርት ኦቭ ዲቫይን ጀስቲስ? ፈረንሳይኛ:- ጋይዳንስ ኦቭ ጐድ፤ የ2000 ንቁ! ጥራዝ።
◼ በድጋሚ የደረሱን፦ አረብኛ:- እውቀት፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው። እንግሊዝኛ:- መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ የዳንኤል ትንቢት፤ እውቀት፤ መጽሐፌ፤ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፤ ጀሆቫስ ዊትነስስ ኤንድ ኤዱኬሽን፤ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 30-85፤ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (bi12)፤ ሰብሚሽን፤ የቴፕ ክሮች:- የቤተሰብ ደስታ፣ መጽሐፌ፣ ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ 1 ሳሙኤል፣ 2 ሳሙኤል፣ 1 ነገሥት፣ 2 ነገሥት፣ 1 ዜና መዋዕል፣ 2 ዜና መዋዕል፣ ዕዝራ፣ ምሳሌ፣ ሮሜ፣ የውዳሴ መዝሙር (8 ክሮችን የያዘ አልበም)፤ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር፣ ጀሆቫስ ጀጅመንት፤ ሲዲዎች:- የመንግሥቱ ዜማዎች ቁጥር 4, 6, 7፤ የቪዲዮ ክሮች:- ሪል ፍሬንድስ፣ ቱ ዚ ኢንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ። ፈረንሳይኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው።