መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅ. 1, 2001
“አሁን አሁን ብዙ ሰዎች በአምላክ ስለማመን መወያየት አይፈልጉም ቢባል ሳይስማሙ አይቀሩም። ሆኖም ይህ የሆነው ለምንድን ነው? [መልሱን ከሰማህ በኋላ ዕብራውያን 11:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛ እምነት ምን እንደሆነና እምነት ያለን መሆን አለመሆኑ ምን ለውጥ እንደሚያመጣ ይገልጻል።”
ንቁ!® ጥቅ. 2001
“ብዙዎቻችን የሚበላ ነገር እንደልብ የመገኘቱን ጉዳይ እምብዛም ትኩረት ሰጥተን አስበንበት አናውቅም። ሆኖም አሁን አሁን ሳይንስ በምግብ አቅርቦት ላይ አደጋ እየፈጠረ ይሆን የሚል ስጋት አለ። ይህ መጽሔት አሳሳቢ ሆነው የተገኙት አንዳንድ ችግሮች ምን እንደሆኑና ለችግሩ እንዴት እውነተኛ መፍትሔ እንደሚገኝ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ተስፋ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥቅ. 15, 2001
“የተሻለና ደስታ የሰፈነበት ዓለም ለማምጣት የሚቻለው እንዴት ነው? [ምላሽ እንዲሰጥ ፍቀድለት] የሰው ልጅ የተሻለ ዓለም ለማምጣት የተለያዩ የአገዛዝ ዓይነቶችን ሞክሯል። ሆኖም አምላክ ስለዚህ ጉዳይ ያለውን አመለካከት እስቲ እንይ። [ኤርምያስ 10:23ን አንብብ] በዚህ መጽሔት ላይ የሚገኘው ይህ ርዕስ ‘ደስታ የሰፈነበት ዓለም እንዴት’ በቅርቡ እንደሚመጣ ያብራራል።”