ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ በሚከተሉት ጉባኤዎች አዲስ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ሥራ በቅርቡ ተጠናቋል:- አዋሳ፣ ጊንጪ፣ ጎባ፣ መቱ፣ ሚዛን፣ ሞጆ እና ናዝሬት። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ 45 የሚሆኑ ተሠርተው የተጠናቀቁ የመንግሥት አዳራሾች አሉን።
◼ ባለፈው ዓመት የሚከተሉት አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል:- አዲስ አበባ አስኮ፣ አየለ (ፊንጫ አቅራቢያ)፣ ባኮ፣ በለስቶ (አለታ ወንዶ አቅራቢያ)፣ ጫኖ (አርባ ምንጭ አቅራቢያ)፣ ፍቼ፣ ኢሎ (ወሊሶ አቅራቢያ)፣ ከሚሴ፣ ለኩ (አዋሳ አቅራቢያ)፣ መቂ፣ ኦፋገንዳባ (ሶዶ አቅራቢያ)፣ ሻሸመኔ ደቡብ፣ ጢስአባሊማ (በደሴ እና በወልድያ መካከል) እና ወንዶ ጢቃ (አዋሳ አቅራቢያ)። ይህ የጉባኤዎችን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 107 ከፍ ያደርገዋል።
◼ በተከታታይ ባደረግናቸው 16 የወረዳ ስብሰባዎች ላይ በድምሩ 8,874 የሚደርስ ከፍተኛ የተሰብሳቢ ቁጥር የተገኘ ሲሆን 79 ተጠማቂዎች ነበሩ። በተጨማሪም 20 የልዩ ስብሰባ ቀኖች የነበሩን ሲሆን 8,819 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል። ከእነዚህ ውስጥ 63 ሰዎች ተጠምቀዋል።