የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/02 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 2/02 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ራእይ​—⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም ጉባኤው ያለውን ማንኛውንም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። በእንግሊዝኛ ሕይወት​—⁠እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽ​ሔቶች። በተመላልሶ መጠይቅ ወቅት ሰውዬው ፍላጎት እንዳለው ከተገነዘብን ኮንትራት እንዲገባ መጋበዝ እንችላለን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ።

◼ በልዩ የአገልግሎት ክልል ዘመቻ ወቅት አስፋፊዎች እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ማበርከት ይችላሉ። የቤቱ ባለቤት እነዚህ ሁለት ጽሑፎች ካሉት ማንኛውንም ሌላ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል። ሁሉም ቤታቸው ላልተገኙ ሰዎች የሚተዉት ወይም ጽሑፍ ለማይወስዱ ሰዎች የሚያበረክቱት የተለያዩ ትራክቶች መያዝ ይኖርባቸዋል። በተለይ ለማንም ባልተመደቡ ክልሎች አቅራቢያ ጉባኤ በሚኖርበት ጊዜ ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተከታትሎ ለመርዳት ጥረት መደረግ ይኖርበታል።

◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2002 ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 14 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “‘አስፈሪውን ቀን’ በአእምሯችሁ አቅርባችሁ ተመልከቱ” የሚል ነው። የንግግሩ አስተዋፅኦ ይላክላችኋል። በዚህ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 14, 2002 በፊት ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።

◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማ​ግኘት የማኅበሩን ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ። እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎታችን 9-68 ገጽ 5 አንቀጽ 12-20ን ተመልከቱ።

◼ ጸሐፊው ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች የቀረበ መጠይቅ ቅጽ (S-82) የሞሉትን የተጠመቁ አስፋፊዎች ሁኔታ በሚመለከት የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ዴስክ ወቅታዊ መረጃ ያለው መሆኑን መከታተል አለበት። በፈቃደኛ ሠራተኛው ሁኔታ ላይ ለውጥ ካለ ማለትም ወደ ሌላ ጉባኤ ከሄደ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ሆኖ ከተሾመ ወዲያውኑ አዲስ ቅጽ ተሞልቶ መላክ ይገባዋል። ፈቃደኛ ሠራተኛው የፖስታ ሣጥን ቁጥር ወይም ስልክ ቁጥር ከለወጠ ወይም በጉባኤ ውስጥ እንደ ቀድሞው በጥሩ አቋም ላይ የማይገኝ ከሆነ ሽማግሌዎች ወዲያውኑ ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ዴስክ በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

◼ በ2002 ለሚደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች የወጣ ጊዜያዊ ፕሮግራም:-

መስከረም 27-29:- አዲስ አበባ (በእንግሊዝኛ ብቻ)

ጥቅምት 11-13:- አዲስ አበባ (የምልክት ቋንቋን ይጨምራል።)

ጥቅምት 18-20:- ድሬዳዋ

ጥቅምት 27-29:- ጅማ

ጥቅምት 27-29:- መቀሌ

ኅዳር 1-3:- ደሴ

ኅዳር 1-3:- ነቀምቴ

ኅዳር 8-10:- ሻሸመኔ

ኅዳር 9-10:- ጊምቢ (በኦሮምኛ ብቻ)

ኅዳር 9-10:- አርባ ምንጭ (በወላይትኛ ብቻ)

ኅዳር 16-17:- ይርጋለም (በሲዳምኛ ብቻ)

ኅዳር 15-17:- ሶዶ

ኅዳር 15-17:- ባህር ዳር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ