የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/02 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 3/02 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። አስፋፊዎች መጽሔት ያበረከቱለት ሰው ለዓለም አቀፉ ሥራ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችል ሊነግሩት ይገባል። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር በማበርከት የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ጉባኤው ያለውን ሌላ ተስማሚ የሆነ ብሮሹር አበርክቱ።

◼ በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ከአሁኑ እቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው ማስገባት አለባቸው። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት እንዲያመቻቹ እንዲሁም የመጽሔቶችና የሌሎች ጽሑፎች በቂ አቅርቦት እንዲኖር እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል። በረዳት አቅኚነት እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው ሁሉ በየወሩ ስማቸው ለጉባኤው መነገር አለበት።

◼ የመታሰቢያው በዓል ሐሙስ መጋቢት 28, 2002 ይከበራል። ጉባኤያችሁ ሐሙስ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ ስብሰባው የመንግሥት አዳራሹ ነጻ ወደሆነበት ሌላ የሳምንቱ ቀን ይዛወራል። ይህ ካልተቻለና የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራሙ ሳይሸፈን የሚቀር ከሆነ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑት ክፍሎች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ ይቻላል።

◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማሳወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። የትኞቹ ጽሑፎች በልዩ ትእዛዝ እንደሚገኙ እባካችሁ አትርሱ።

◼ የጽሑፍ መላኪያ ክፍላችን ስልክ ቁጥር ወደ 63 26 87 መለወጡን እንገልጽላችኋለን።

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ ማውጫ 1986-2000 (በአንድ ጥራዝ)፤ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? (ትራክት ቁጥር 26)፤ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2002። ፈረንሳይኛ፦ የ2002 የቀን መቁጠሪያ፤ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? (ትራክት ቁጥር 26)። ትግርኛ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2002።

◼ በድጋሚ የደረሱን፦ አማርኛ፦ መጽሐፌ፤ መጽሐፍ ቅዱስ​—⁠የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ የውዳሴ መዝሙር፤ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ ስንሞት ምን እንሆናለን?፤ እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?፤ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ። እንግሊዝኛ፦ የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል፤ ኮንኮርዳንስ፤ እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፤ አወር ፕሮብሌምስ፤ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?። ኦሮምኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ