ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ፍላጎት ያሳየ ሰው ስታገኙ የመጽሔት ደንበኛችሁ አድርጉት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱለት። ሰኔ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ጉባኤው ያለውን ሌላ ተስማሚ የሆነ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል። ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?
◼ በዓመቱ ውስጥ የምትጠቀሙባቸው የጉባኤ ቅጾች በግንቦት ወር ከሚላከው ጽሑፍ ጋር ይላክላችኋል። ቅጾቹ የሚከፋፈሉበትን መንገድ በተመለከተ መመሪያዎች በጽሑፍ መላኪያ ዝርዝሩ ላይ ይኖራሉ።
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ አንዳንዶች ለአዲሱ የቤቴል ግንባታ ፕሮጀክት እንዴት የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችሉ ጠይቀዋል። እንዲህ ያሉትን መዋጮዎች ከልብ እናደንቃለን። እነዚህን መዋጮዎች ለዓለም አቀፉ ሥራ ከሚደረገው መዋጮ ጋር ጨምሮ መላክ ወይም “ለአዲሱ የቤቴል ግንባታ ፕሮጄክት” በማለት በባንክ ሒሳባችን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። ይህን በተመለከተ ከጉባኤው ጸሐፊ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል። በግንባታው ሥራ በጉልበት ለመርዳት የሚፈልጉ ወንድሞችና እህቶችም አሉ። ይህ የሚያስመሰግን ነው። ይሁን እንጂ ግንባታው የሚካሄደው በግል የሕንጻ ተቋራጭ በመሆኑ ከጥንቃቄ ሕጎችና ከኢንሹራንስ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች ስላሉ ፈቃደኛ ሠራተኞችን በግንባታ ሥራው ማሳተፍ እንደሚያስቸግር ትገነዘባላችሁ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
◼ ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራና ለማኅበሩ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ሥራ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቼክ ፈርመው በጉባኤ የአስተዋጽኦ ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩ ካሉ ክፈል በሚለው የቼኩ ክፍት ቦታ ላይ መጻፍ ያለባቸው “የይሖዋ ምሥክሮች” ወይም “Jehovah’s Witnesses” ብለው ነው። በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በቼክ የሚደረጉ ወይም ለቅርንጫፍ ቢሮው የሚላኩ መዋጮዎችም መጻፍ ያለባቸው በተመሳሳይ ሁኔታ ነው።
◼ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ አዳዲስ ሰዎች አስፋፊ ሆነዋል። እነዚህ አስፋፊዎች የይሖዋ ምሥክሮች በኢትዮጵያ—ነፃነት አፍቃሪዎች የተባለው ስላለፈው ታሪካችን ልብ የሚነኩና ጠቃሚ የሆኑ ዘገባዎችን የያዘው የአማርኛ ብሮሹር ደርሷቸዋል? ተጨማሪ ቅጂዎች ካስፈለጓችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ የሚያዝያ 2002 ንቁ! መጽሔት (በእንግሊዝኛ መጋቢት 8, 2002) ስለ መምህርነት ሙያ የሚናገሩ ግሩም የሆኑ ርዕሶችን ይዟል። ተማሪዎች፣ ወላጆችና ሌሎች አስፋፊዎች በትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ይህን መጽሔት በስፋት ለማሰራጨት ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ እናበረታታቸዋለን። በቅርንጫፍ ቢሮው ውስጥ ይህ መጽሔት በበቂ መጠን ስለሚገኝ ተጨማሪ ቅጂዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ።