ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን? የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? መስከረም፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ።
◼ ከመስከረም 16, 2002 ጀምሮ በእንግሊዝኛ ጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን የተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2 ይሆናል።
◼ ከመስከረም ወር ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ክርስቲያን መሆናችሁ ሁልጊዜ ግልጽ ሆኖ ይታይ!” የሚል ይሆናል።