ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ሌላ የቆየ መጽሐፍ ልናበረክትላቸው እንችላለን። ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ —የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉትን መጻሕፍት በአማራጭነት መጠቀም ትችላላችሁ።
◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።
◼ አዲስ የደረሱን:- አረብኛ:- የኢሳይያስ ትንቢት—ጥራዝ ሁለት። ፈረንሳይኛ:- የአገልግሎት ትምህርት ቤት።
◼ በድጋሚ የደረሱን:- አማርኛ:- መጽሐፍ ቅዱስ —የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ ወጣትነትህ። እንግሊዝኛ:- የአገልግሎት ትምህርት ቤት፤ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ፤ የ2000 የዓመት መጽሐፍ፤ ንቁ! ጥራዞች 1994, 1995፤ መጠበቂያ ግንብ ጥራዝ 1987፤ የኅዳር 1990 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ፤ ትራክቶች:- T-19፤ T-20፤ T-21፤ T-22፤ T-24፤ T-71፤ T-72። ወላይትኛ:- ትራክቶች:- T-13፤ T-14፤ T-15፤ T-16።