የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/02 ገጽ 8
  • ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 10/02 ገጽ 8

ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?

1 ትናንሽ ልጆችም ጭምር መጠመቅ አለባቸውን? በራእዩ ውስጥ ይሖዋ መሣሪያ ለታጠቁት ስድስት ሰዎች የሚከተለውን መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር:- “ሽማግሌውንና ጎበዙን፣ ቆንጆይቱንም፣ ሕጻናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ።” (ሕዝ. 9:6) እርግጥ ራሳቸውን ለመወሰን ያልደረሱ ትናንሽ ልጆች ወላጆቻቸው ይሖዋን እንዲወዱ አድርገው እያሳደጓቸው ከሆነና ልጆቹ በታዛዥነት ለውጥ ካደረጉ በወላጆቻቸው ላይ ባለው “ምልክት” መሠረት ከጥፋቱ ይጠበቃሉ። (1 ቆ⁠ሮ. 7:14) ነገር ግን ልጁ የግል ውሳኔ ለማድረግ በቂ ማስተዋል ካለውና ‘በጎ ማድረግ ወደሚያውቅበት’ ደረጃ ከደረሰ በወላጆቹ “ምልክት” ለሁልጊዜው ተጠልሎ ይኖራል ብላችሁ አታስቡ።​—⁠ያዕ. 4:17

2 አንድ ትንሽ ልጅ ራሱን ከመወሰኑ በፊት ነገሩ ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባው በቂ እውቀት ሊኖረው እንዲሁም ከአምላክ ጋር የግል ዝምድና የመመሥረት ፍላጎት ሊያዳብር ይገባል። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መረዳትና ከእነርሱም ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲሁም ቢጥሳቸው ተጠያቂ እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልገዋል። በተጨማሪም እምነቱን ለሌሎች በማካፈል ረገድ በቂ ተሞክሮ ሊኖረውና ይህ ሥራ የእውነተኛ አምልኮ አንዱ ትልቅ ክፍል መሆኑን ሊያውቅ ይገባዋል። አምላክን ለማገልገል ልባዊ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል። የትልቅ ሰውን ያህል ጉልምስና እንዲያሳይ አይጠበቅበትም፣ ቢሆንም መንፈሳዊ እድገቱ በእርሱ ደረጃ ወደፊት እየቀጠለ የሚሄድ መሆን አለበት።

3 አንድ ትንሽ ልጅ ‘ወጪውን አስልቶ’ ከሆነ ራሱን ቢወስን ምንም ጉዳት አይደርስበትም። በአብዛኞቹ አዳዲስ ክርስቲያኖች እንደታየው ሁሉ ከጥምቀት በኋላ አድናቆታቸው ጥልቀት ያለው ይሆናል። ዴቪድ የተባለ አንድ ወጣት እንዲህ ብሏል:- “በልጅነቴ መጠመቄ ጥበቃ ሆኖልኛል። እያደግሁ ስሄድ በጉባኤው ውስጥ ያሉ አንዳንድ ያልተጠመቁ ልጆች ከሽማግሌዎቹ ሥልጣን ነጻ እንደሆኑ እንደተሰማቸውና ከዚህ የተነሳ ወደ መጥፎ አድራጎት እንደገቡ ተመልክቻለሁ። እኔ ግን ሕይወቴን ለአምላክ እንደወሰንኩ ሁልጊዜ አስታውስ ነበር። ሕይወቴ የአምላክ ንብረት ነው። ስለዚህ እንደነዚህ ያሉትን ወጣቶች ለመከተል አልቻልኩም።”

4 ‘ልጄ ገና በትንሽነቱ ተጠምቆ (ተጠምቃ) በኋላ ቢቀዘቅዝስ (ብትቀዘቅዝስ)?’ በማለት አንዳንድ ወላጆች ይጠይቃሉ። እርግጥ ነው አንድ ወጣት ልጅ ወላጆቹን ለማስደሰት ብቻ ወይም ጓደኞቼ አድርገውታል ብሎ መጠመቅ የለበትም። ይሁን እንጂ ዮሴፍ፣ ሳሙኤል፣ ንጉሥ ኢዮስያስና ኢየሱስ ገና በልጅነታቸው የይሖዋን አምልኮ በቁምነገር ተመልክተው አጥብቀው ይዘውታል።​—⁠ዘፍ. 37:2፤ 39:1-3፤ 1 ሳ⁠ሙ. 1:24-28፤ 2:18-21፤ 2 ዜ⁠ና 34:3፤ ሉቃስ 2:42-49

5 በዘመናችን ዣን የተባለች አንዲት ክርስቲያን የተጠመቀችው በአሥር ዓመቷ ነበር። ከጊዜ በኋላ የወሰደችው እርምጃ ገብቷት እንደነበረ ስትጠየቅ ዣን “ይሖዋን እንደምወድ አውቅ ነበር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገልንን አደንቅ ነበር፣ ስለዚህ ይሖዋን ለማገልገል ፈለግኩ” ብላ መል​ሳለች። ከጥምቀቷ በኋላ ከ40 ለሚበልጡ ዓመታት በታማኝነት አገልግላለች። በአገራችንም በትንሽነታቸው የተጠመቁ በርካታ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችና አስፋፊዎች አሉ። እያንዳንዱ ወጣት ልጅ የተለየ ግለሰብ ነው፣ ማንም ሰው አንድ ቋሚ የዕድሜ ወሰን ማበጀት አይችልም። ወላጆች የልጆቻቸውን ልብ ለመንካት መጣር አለባቸው። ለአምላክ ያደሩ የመሆንን ባሕርይ እንዲያዳብሩ ሊረዷቸው ይገባል። በልጆቹ ፊት ራስን የመወሰንንና የመጠመቅን መብት ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ የማይነቃነቁ አምላኪዎች እንዲሆኑ ሊያጠናክሯቸው ይገባል።​—⁠3 ዮሐ. 4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ