የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ኅዳር 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 82 (183)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ ማካሄጃ ገንዘብ እንዴት እንደሚገኝ ተናገር።—መጠበቂያ ግንብ ገጽ 2 ላይ ወይም ንቁ! ገጽ 5 ላይ ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “ልማድ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለበጎ ተጠቀሙበት።” በነሐሴ 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 19-22 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻችሁ ጋር ተባበሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች ሆኖ በሚያገለግል ሽማግሌ ይቀርባል። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 70 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። የጉባኤው አባላት የመጽሐፍ ጥናት ዝግጅትን እንደሚደግፉ ያሳዩባቸውን የተለያዩ መንገዶች በመጥቀስ አመስግናቸው፤ እንዲሁም ማሻሻያ ማድረግ የሚያስፈልግባቸውን መስኮች በደግነት ጠቁም።
መዝሙር 49 (114) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 79 (177)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። (የመጀመሪያውን።) ጥሩ ችሎታ ባለው ሽማግሌ በንግግር የሚቀርብ።
25 ደቂቃ:- “እናንት የቤተሰብ ራሶች—ቤተሰባችሁ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ እንዲያዳብር እርዱት።” በአንቀጽ 1-3 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርተህ አጭር የመግቢያ ንግግር ካደረግህ በኋላ ከ4-13 ያሉትን አንቀጾች ከአድማጮች ጋር ተወያዩባቸው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አንቀጽ 7, 8, 11 እና 12ን አንብብ። ከአንድ ወይም ሁለት ወላጆች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ቤተሰባቸው ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ እንዲኖረው የረዳው ምንድን ነው? እንዲህ ለማድረግ ምን ጥረት ጠይቆባቸዋል? ምንስ ጥቅም አግኝተዋል? ከአንቀጽ 14 ላይ አጠር ያሉ ሐሳቦችን በመናገር ደምድም።
መዝሙር 32 (70) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አብረው የሚያገለግሉ ባልና ሚስት በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በሠርቶ ማሳያ ያቀርባሉ። ባልየው መጠበቂያ ግንብ ሲያበረክት ሚስት ደግሞ ንቁ! ታበረክታለች።
15 ደቂቃ:- “ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት አስታውቁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 278 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “‘አባት ለሌላቸው ልጆች’ ፍቅራዊ አሳቢነት አሳዩአቸው።” ይሖዋ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች የሚያይበትን መንገድ በተመለከተ በአንደኛው አንቀጽና ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 816 ላይ የተመሠረተ የሦስት ደቂቃ ንግግር በማድረግ ጀምር። ከዚያም ቀሪዎቹን አንቀጾች በጥያቄና መልስ ተወያዩባቸው። ሌሎች እርዳታና ማበረታቻ ሊሰጡ የሚችሉባቸውን ተግባራዊ መንገዶች ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንቀጽ 3 እና 4ን ስትወያዩ ከጥቅምት 8, 1995 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 8, 9 ላይ አጠር ያሉ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የሚረዳ አንድ ሠርቶ ማሳያ በአጭሩ ተናገር።—የሰኔ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ10ን ተመልከት።
12 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። (ሁለተኛውን።)
25 ደቂቃ:- “ከሁሉ ለላቀው ሥራ የሚያስታጥቀን ትምህርት ቤት።” የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ሁሉም በጥር ወር የሚጀምረውን አዲሱን የትምህርት ቤት ፕሮግራም በጉጉት እንዲጠባበቁት አድርግ። “የ2003 የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ከሚለው ከጥቅምት 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ አንዳንድ የትምህርት ቤቱን ገጽታዎች ተናገር። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 282 ላይ የሰፈሩትን በትምህርት ቤቱ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ብቃቶችን ዘርዝር፤ እንዲሁም ብቃቱ እያላቸው ሆኖም እስካሁን ያልተመዘገቡ ካሉ እንዲመዘገቡ አበረታታ።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።