የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/02 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 11/02 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ሌላ የቆየ ጽሑፍ ልናበረክትላቸው እንችላለን። በጉባኤያችሁ ውስጥ የቆዩ ጽሑፎች ከሌሉ ከአጎራባች ጉባኤዎች መጠየቅ ትችላላችሁ። ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። በአማራጭነት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ​—⁠የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉትን መጻሕፍት መጠቀም ትችላላችሁ። ጥር:- ጉባኤው ያለውን ማንኛውንም ከ1988 በፊት የታተመ ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። እነዚህ ጽሑፎች በጉባኤያችሁ ውስጥ ከሌሉ ከአጎራባች ጉባኤዎች ጠይቁ።

◼ ታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።

◼ ጉባኤዎች በታኅሣሥ ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2002 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ጥራዞቹን በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣልያንኛ እና በስፓንኛ ማግኘት ይቻላል። ጥራዞቹ ደርሰውን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይገለጻል። ጥራዞች በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ጽሑፎች ናቸው።

◼ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች በትልቅ ወረቀት ጽፋችሁ እስከ ታኅሣሥ 31, 2002 ድረስ ልትልኩልን ትችላላችሁ:- 1) ስም 2) ዕድሜ 3) የተጠመቁበት ቀን 4) የጋብቻ ሁኔታ [ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት] 5) ለማገልገል የምትችልባቸው ወራት [ከመጋቢት እስከ ግንቦት?] 6) የምትናገራቸው ቋንቋዎች 7) አመልካቹ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ አዘውትሮ የሚካፈል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት የድጋፍ ሐሳባቸውን ካሰፈሩ በኋላ ይፈርሙበታል።

◼ በየካቲት ወር ፌዝፉል አንደር ትራያልስ​—⁠ጂሆቫስ ዊትነስስ ኢን ዘ ሶቪየት ዩኒየን የተባለው የቪዲዮ ፊልም በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይከለሳል። የዚህን ቪዲዮ ቅጂ ለማግኘት የሚፈልጉ አሁኑኑ በጉባኤያቸው በኩል ትእዛዝ መላክ አለባቸው።

◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- እውቀት። እንግሊዝኛ:- ክሪኤተር፣ ኤዱኬሽን፣ ሳትስፋይንግ ላይፍ፣ የዳንኤል ትንቢት፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የሙታን መናፍስት፣ የ2001 ጥራዞች፣ ከ1930-1985 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ