የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/03 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 1/03 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ጥር:- “መንግሥትህ ትምጣ፣” ወጣትነትህ፣ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው እንደሚሉት ያሉ የቆዩ መጽሐፎችን ማበርከት ይቻላል። የካቲት:- ራእይ —⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ሚያዝያ እና ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች።

◼ ከየካቲት ወር ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲስ የሕዝብ ንግግር “በጨለማ የተዋጠው ዓለም ከሚደርስበት ጥፋት መዳን” የሚል ይሆናል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ረቡዕ ሚያዝያ 16 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት በአቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። ቂጣውና ወይኑ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በእጅ እየተቀባበሉ ለማሳለፍ በሚመቻቸው ዕቃ መቅረብ አለበት። የወይኑን ዓይነት በተመለከተ ከቀይ ወይን የተጠመቀውና ምንም ዓይነት ማጣፈጫ ያልገባበትን ዱከም ወይን ጠጅን ወይም ከውጭ አገር የሚመጡ ተመሳሳይ ቀይ ወይኖችን እንድትጠቀሙ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። በገለልተኛ ክልሎች ያሉ ቡድኖች የራሳቸውን ወይን ለማዘጋጀት የሚገደዱ ከሆነ በየካቲት 15, 1990 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18 (መጠበቂያ ግንብ 4-111 ገጽ 16) ላይ እና በመስከረም 8, 1995 (የእንግሊዝኛ) ንቁ! ገጽ 25-27 ላይ ያሉትን መመሪያዎች መመልከት አለባቸው። ብዙ ጉባኤዎች በአንድ ላይ ሆነው የመታሰቢያውን በዓል በሚያከብሩበት ወቅት ማን የየትኛው ጉባኤ እንግዳ እንደሆነ ለመለየት አስቸጋሪ ስለሚሆን እንዲህ ማድረጉ አይበረታታም። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን ለማድረግ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ሁለት ወይም ሦስት ጉባኤዎች ካሉ አንዱ ወይም ሁለቱ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታዎችን መፈለግ ይችሉ ይሆናል። ሁለት ጉባኤዎች በአንድ አዳራሽ ተራ በተራ የመታሰቢያውን በዓል ለማክበር ዝግጅት በሚያደርጉበት ጊዜ ሁሉም ከአጋጣሚው ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። (ለምሳሌ ያህል የመጀመሪያው ስብሰባ በ12:​00 ሰዓት የሚጀምር ከሆነ ሁለተኛው ስብሰባ በ1:​30 ይጀምራል።) ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።

◼ ከዚህ ወር እትም ጀምሮ አዲስ የደረሱንን ጽሑፎች የያዘ ዝርዝር በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ አይወጣም። ይህን መረጃ የያዘ “ለሁሉም ጉባኤዎች የሚሆን ማስታወቂያ” ለጉባኤዎች ይላካል። ጉባኤዎች ይህ ማስታወቂያ ሲደርሳቸው በቀጣዩ ሳምንት በሚያደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ከዝርዝሩ ውስጥ ለጉባኤው የሚያስፈልጉት ጽሑፎች በማስታወቂያ ይነገራሉ። ከዚያም ማስታወቂያው በማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ ይለጠፋል። በኋላም የጽሑፍ አገልጋዩ በፋይሉ ውስጥ ሊያስቀምጠው ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ