ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 24, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 6 እስከ የካቲት 24, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. እውነት ወይም ሐሰት:- እየተነበበ ያለው ነገር በጽሑፉ ላይ ካለው ትንሽ ለየት ቢልም እንኳን ለሰሚው ትክክል እስከመሰለ ድረስ ጥርት ያለ ንባብ ነው ለማለት ይቻላል። አብራራ። [be ገጽ 83]
2. ባዶ ቦታውን ሙላ:- ጥርት አድርጎ ለማንበብ ድምፅን ከፍ አድርጎ _________________________ ያስፈልጋል። [be ገጽ 84]
3. ቃላትን አጥርቶ መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (1 ቆሮ. 14:8, 9) [be ገጽ 86]
4. ቃላት በግልጽ እንዳይሰሙ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? አጥርቶ ለመናገርስ ምን ማድረግ ይቻላል? [be ገጽ 87-8]
5. ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ የሰማሃቸው ትክክለኛ አጠራራቸውን መለማመድ የሚያስፈልግህ አንዳንድ ቃላት የትኞቹ ናቸው? [be ገጽ 92]
ክፍል ቁ. 1
6. እውነት ወይም ሐሰት:- ዓይናችን በጥሩ ሁኔታ እንድናዳምጥ ይረዳናል። አብራራ። [be ገጽ 14]
7. ባዶ ቦታውን ሙላ:- ___________________________________፣ _________________________ እና _________________________ አምላክ የሰጠን የጊዜ መለኪያዎች ናቸው። [si ገጽ 279 አን. 7]
8. ባዶ ቦታውን ሙላ:- መጽሐፍ ቅዱስ “ቀን” የሚለውን ቃል ________________________________ ሰዓት፣ _______________________________ ሰዓት፣ _____________________ ዓመት ወይም _________________________ ለማመልከት የሚጠቀምበት ሲሆን የቃሉን ትርጉም የሚወስነው አገባቡ ነው። [si ገጽ 279 አን. 8]
9. የሐና፣ የማርቆስና የኤልያስ ምሳሌ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን እንድንቋቋም ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? በእነዚህ ምሳሌዎች ተጠቅመን ሌሎችን እንዴት መርዳት እንችላለን? [w01 2/1 ገጽ 20-3]
10. በጥንት ዘመን ይካሄዱ ስለነበሩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ግንዛቤ ማግኘታችን አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በግልጽ እንድንረዳ የሚያደርገን እንዴት ነው? ይህ እውቀት ሕይወታችንን እንዴት ሊነካው ይገባል? [w01 1/1 ገጽ 28-31]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. እውነት ወይም ሐሰት:- የአምላክ መንግሥት በ1914 በሰማይ ስለተቋቋመ ከዚያ በኋላ “መንግሥትህ ትምጣ” ብሎ መጸለይ ተገቢ አይደለም። (ማቴ. 6:10) አብራራ። [be ገጽ 279፤ w96 6/1 ገጽ 31]
12. እውነት ወይም ሐሰት:- በማቴዎስ 11:24 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ ይሖዋ በእሳት ያጠፋቸው በሰዶምና በገሞራ የነበሩ ሰዎች ትንሣኤ እንደሚያገኙ ያሳያል። አብራራ።
13. ምርጫ:- ኢየሱስ በማቴዎስ 24:45-47 ላይ የጠቀሰው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? (ሀ) የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል፤ (ለ) በማንኛውም ጊዜ በቡድን ደረጃ በምድር ላይ የሚገኙ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በሙሉ፤ (ሐ) ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ። ይህ ባሪያ ‘ለቤተሰቦቹ’ በተገቢው ጊዜ መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል፤ ቤተሰቡ የተባሉት እነማን ናቸው? (ሀ) በግለሰብ ደረጃ የሚገኙ ቅቡዓን ክርስቲያኖች፤ (ለ) ሌሎች በጎች፤ (ሐ) ክርስቲያናዊ ጽሑፎችን የሚያነብቡ ሰዎች በሙሉ። ጌታው ባሪያውን በንብረቱ ሁሉ ላይ የሾመው መቼ ነው? (ሀ) በ1914፤ (ለ) በ33 እዘአ፤ (ሐ) በ1919።
14. ምርጫ:- ኢየሱስ በማቴዎስ 13:47-50 ላይ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው መረብ ከቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ ሌላ ማንን ይጨምራል? (ሀ) የአምላክን መሲሐዊ መንግሥት፤ (ለ) አጋሮቻቸው የሆኑትን ሌሎች በጎች፤ (ሐ) ሕዝበ ክርስትናን።
15. በማቴዎስ 5:24 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው የኢየሱስ ቃል መሠረት የእምነት ጓደኛህን እንዳስቀየምከው ከተሰማህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? [g96 2/8 ገጽ 26-7]