ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 28, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 3 እስከ ሚያዝያ 28, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. ቅልጥፍና እንዳይኖር እንቅፋት የሚሆኑት ምክንያቶች የትኞቹ ሊሆኑ ይችላሉ? [be ገጽ 93]
2. እውነት ወይም ሐሰት:- ቆም ማለት የሰዎች ሐሳብ እንዲከፋፈል ሊያደርግ ስለሚችልና ውይይቱን ለማስቆም አጋጣሚ ስለሚሰጣቸው አስፈላጊ አይደለም። አብራራ።
3. ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ ማጥበቅ ለአንድ ተናጋሪ ወይም አንባቢ ምን ጠቀሜታ አለው? (ነህ. 8:8) [be ገጽ 101]
4. አንድ ተናጋሪ ወይም አንባቢ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ ማጥበቅን ማዳበር የሚችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 102-3]
5. በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት ወይም በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሲነበብ አጽንኦት ሊሰጣቸው የሚገቡት ዋና ዋና ነጥቦች የትኞቹ ናቸው? [be ገጽ 105]
ንግግር ቁ. 1
6. ወላጆች ልጆቻቸው በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ “ይሰሙና ይማሩ ዘንድ” ለማሰልጠን ምን ማድረግ ይችላሉ? (ዘዳ. 31:12) [be ገጽ 16]
7. መንፈሳዊ ገነት ምንድን ነው? [w 01 3/1 ገጽ 8-10]
8. ምሳሌ 8:1-3 ማንኛውም ሰው አምላካዊ ጥበብ ማግኘት እንደሚችል የሚያሳየው እንዴት ነው? በቆላስይስ 2:3 መሠረት ይህን ጥበብ ማግኘት የሚቻለው የት ነው? [w 01 3/15 ገጽ 25, 28]
9. የአምላክን ስም ለሰዎች ማሳወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (ዮሐንስ 17:6) [be ገጽ 273-5]
10. ሰዎች ‘የመንግሥቱን ወንጌል’ በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡት ዐቢይ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? (ማቴ. 24:14) [be ገጽ. 279-80]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. (ሀ) በማርቆስ 13:14 ላይ የተጠቀሰው “ርኩሰት” በመጀመሪያው መቶ ዘመን ምንን ያመለክት ነበር? (ለ) ‘በማይገባ ስፍራ መቆሙ’ ምን ያመለክት ነበር?
12. ኢየሱስ የዳዊት ዙፋን ወራሽ መሆኑን የሉቃስ ወንጌል የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? (ሉቃስ 3:23-38) [w92 10/1 ገጽ 10 አን. 3]
13. ሉቃስ 12:2 ላይ ሠፍሮ የሚገኘው የኢየሱስ አባባል ምን ትርጉም አለው?
14. ኢየሱስ ስለ ጠፋው ድሪም በተናገረው ምሳሌ ላይ መላእክት ድሪሙ በመገኘቱ መደሰታቸው አስደናቂ የሆነው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 15:10) የእነርሱ ምሳሌ እኛን እንዴት ሊነካን ይገባል?
15. ሉቃስ 22:29 [NW ] ላይ የተጠቀሱት ሁለት ቃል ኪዳኖች የትኞቹ ናቸው?