ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ለተገኙ ሆኖም ከጉባኤው ጋር አዘውትረው ለማይሰበሰቡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሰኔ:- እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ይበረከታል። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ጉባኤው ያለውን ሌላ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት።
◼ በቋሚነት በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን የይሖዋ ምሥክሮች በኢትዮጵያ—ነፃነት አፍቃሪዎች የተሰኘውን ታሪካዊ ብሮሹር እንዲያነብቡ ማበረታታት ይቻላል። ጉባኤያችሁ የዚህ ብሮሹር በቂ ቅጂዎች ከሌሉት በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ትእዛዛችሁ ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ በ2003 ለሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ የሚሆኑ ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች በቅርቡ ይላኩላችኋል። ካርዶቹ በጉባኤያችሁ የአስፋፊዎች ቁጥር ልክ ስለሚላኩ ማዘዝ አያስፈልጋችሁም። ጉባኤዎች ተጨማሪ ካርድ ካስፈለጋቸው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርባቸዋል። የካርድ መያዣ ፕላስቲክ ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ አለባቸው።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችንና የጸሐፊዎችን ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘቱ አስፈላጊ ነው። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) በፍጥነት ሞልቶና ፈርሞ ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b-AM) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቃ ይኑራችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾች ሙሉ በሙሉ መሞላታቸውን ለማየት በደንብ ተመልከቷቸው። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን መገመትና መዝግበው መያዝ አለባቸው።
◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት በዚያ አገር ሥራውን በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ በቅርቡ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የሚከተሉትን ቅጾች በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ አስፋፊዎች በቀላሉ ሊያገኙት በሚችሉበት ቦታ እንዲያስቀምጡ ልናስታውሳቸው እንወዳለን:- የመስክ አገልግሎት ሪፖርት (S-4-AM)፣ የጥናት ሪፖርት (S-3-AM)፣ ከቤት ወደ ቤት መመዝገቢያ (S-8-AM)። ቅጾቹን ለሪፖርት መሰብሰቢያ ከተዘጋጀው ሣጥን አጠገብ ማስቀመጡ የተሻለ ነው። እርግጥ አስፋፊዎች ሪፖርታቸውን ለመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻቸው በቀጥታ ሊሰጡት ይችላሉ። ከዚህ ቀደም በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት እነዚህን ቅጾች ለተዘጋጁበት ዓላማ ብቻ እንጂ እንደ ማስታወሻ ወረቀት አድርገን ልንጠቀምባቸው አይገባም።
◼ የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናታችሁ የመዋጮ ሣጥን ከሌለው ተስማሚ የሆነና ቁልፍ ያለው ሣጥን እንድታዘጋጁ እናበረታታችኋለን።
◼ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚዘጋጀውን የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ለማግኘት የሚፈልጉ ጉባኤዎች M-202-AM በተባለው ቅጽ ተጠቅመው ትእዛዛቸውን እንዲልኩ እንጠይቃለን። በአገልግሎት ስብሰባ ላይ አዘውትረው የሚገኙ አስፋፊዎችና እድገት እያደረጉ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በፈለጉት ቋንቋ አንድ የመንግሥት አገልግሎታችን ቅጂ መጠየቅ ይችላሉ። አንድ ሰው ከአንድ ቋንቋና ከአንድ ቅጂ በላይ ማዘዝ አይችልም።