ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ለተገኙ ሆኖም ከጉባኤው ጋር አዘውትረው ለማይሰበሰቡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሰኔ:- እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ይበረከታል። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው በጉባኤው ውስጥ የሚገኘውን ሌላ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ”፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት . . .፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ —ሃው ቱ አቴይን ኢት?፣ የሙታን መናፍስት —ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ የኢሳይያስ ትንቢት —ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን የተባለው መጽሐፍ የመጀመሪያው ጥራዝ ተጠንቶ ካለቀ በኋላ ከሰኔ 16, 2003 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 9, 2004 ድረስ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ቀርቧል! የተባለው መጽሐፍ ይሆናል። የጥናቱን ጠቅላላ ፕሮግራም በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። the program will come