ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- ጉባኤው ያለው ከ1988 በፊት የታተመ ማንኛውም መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች ከሌሏችሁ ጎረቤት ጉባኤዎች ትርፍ ይኖሯቸው እንደሆነ ጠይቁ። የቆዩ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የካቲት:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማግኘት ልዩ ጥረት ይደረጋል። የምናነጋግራቸው ሰዎች ይህ መጽሐፍ ካላቸው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። ሚያዝያ:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ይበረከታል። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ለተገኙ ሆኖም ከጉባኤው ጋር አዘውትረው ለማይሰበሰቡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍን እና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “በሕይወታችሁ ውስጥ የላቀ ግምት የምትሰጧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?” የሚል ይሆናል።
◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት እሑድ ሚያዝያ 4 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። በመካከለኛው ኢትዮጵያ ንግግሩን 12:15 ላይ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት በአቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። በዚያ ዕለት ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር ሌላ ስብሰባ ስለማይኖር የመጠበቂያ ግንብ ጥናቱ በሌላ ቀን እንዲካሄድ ተገቢው ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሳምንቱን የስብሰባ ፕሮግራማቸውን እንደ አካባቢው ሁኔታ ማስተካከል ያስፈልጋቸዋል። የሚቻል ከሆነ እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን እንዲያከብር እናበረታታለን። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን ለማድረግ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ሁለት ወይም ሦስት ጉባኤዎች ካሉ አንዱ ወይም ሁለቱ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ ይችሉ ይሆናል። ሁሉም ከአጋጣሚው ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ከተቻለ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንና መጫንን ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።