ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ ጉባኤው ያሉትን እንደ መንግሥትህ ትምጣ እና የአምልኮ አንድነት ያሉ የቆዩ መጽሐፎች።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “የወደፊቱን ጊዜ በእምነትና በድፍረት መጠባበቅ” የሚል ይሆናል።
◼ አስፋፊዎች ለየትኛውም ጉባኤ ባልተመደቡ ክልሎች ውስጥ በሚሠሩበት ወቅት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የቤቱ ባለቤት እነዚህ ሁለት ጽሑፎች ካሉት ማንኛውንም ሌላ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል። ሁሉም አስፋፊዎች ቤታቸው ላልተገኙ ሰዎች የሚተዉት ወይም ጽሑፍ ለማይወስዱ ሰዎች የሚያበረክቱት የተለያዩ ትራክቶች መያዝ ይኖርባቸዋል። በተለይ ለማንም ባልተመደቡት ክልሎች አቅራቢያ ጉባኤ በሚኖርበት ጊዜ ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተከታትሎ ለመርዳት ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b-AM) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቃ ይኑራችሁ።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጾችን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላካቸው በፊት በሚገባ መሞላታቸውን ለማረጋገጥ በደንብ ሊመለከቷቸው ይገባል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን መገመትና መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊም ይህን ቀን በጉባኤ የአስፋፊ ካርድ ላይ ሊመዘግበው ይገባል።
◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የልዩና የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት በዚያ አገር ሥራውን በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ በቅርቡ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችንና የጸሐፊዎችን ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት።