ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 30, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 5 እስከ ነሐሴ 30, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ስለ ተስፋችን ለሚጠይቁን ሰዎች “በትሕትናና በአክብሮት” መልስ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጴጥ. 3:15) [be ገጽ 192 አን. 2-4]
2. በእርግጠኝነት መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ሮሜ 8:38, 39፤ 1 ተሰ. 1:5 የ1980 ትርጉም ፤ 1 ጴጥ. 5:12) [be ገጽ 194]
3. ስለምንናገረው ነገር እርግጠኛ መሆናችን እንዴት ሊታይ ይችላል? [be ገጽ 195 አን. 3–ገጽ 196 አን. 4]
4. በአነጋገር ዘዴኛ መሆን ምን ማለት ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? በአነጋገራችን ዘዴኛ ለመሆን ብለን መልእክታችንን ማለዘብ የሌለብን ለምንድን ነው? (ሮሜ 12:18) [be ገጽ 197]
5. ዘዴኛ የሆነ ሰው ከመናገሩ በፊት ምን ነገር ያስተውላል? (ምሳሌ 25:11፤ ዮሐ. 16:12) [be ገጽ 199]
ክፍል ቁጥር 1
6. ከሌሎች ጋር ስንጫወት የምናወራው ነገር እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ልማዳችን በእውነት ውስጥ ምን ያህል እድገት እንዳደረግን የሚጠቁሙት እንዴት ነው? [be ገጽ 74 አን. 3–ገጽ 75 አን. 2]
7. ‘ዘመኑን በሚገባ መዋጀት’ ሲባል ምን ማለት ነው? ይህንንስ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (ኤፌ. 5:16) [w 02 11/15 ገጽ 22]
8. መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሁሉ በአምላክ ፊት እኩል መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳየው እንዴት ነው? ይህን ማወቃችንስ በአገልግሎታችን ምን እንድናደርግ ሊገፋፋን ይገባል? [w 02 1/1 ገጽ 5, 7]
9. ይሖዋ የሚለው የፈጣሪ ልዩ ስም ምን ትርጉም አለው? [w 02 1/15 ገጽ 5]
10. አቤል ከቃየን ይልቅ “የበለጠ” መሥዋዕት እንዳቀረበ የተገለጸው ለምንድን ነው? ለይሖዋ የምናቀርበውን ‘የምስጋና መሥዋዕት’ በተመለከተ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዕብ. 11:4፤ 13:15) [w 02 1/15 ገጽ 21, 22 አን. 6-8]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዘሌዋውያን 18:3 ትክክልና ስህተት የሆነውን በመለየት ረገድ የተዛባ አመለካከት እንዳይኖረን የሚረዳን እንዴት ነው? (ኤፌ. 4:17-19) (w 02 2/1 ገጽ 29)
12. በዓለ ኀምሳ (ጰንጠቆስጤ) በተባለው በዓል ላይ ሊቀ ካህኑ “ለሚወዘወዝ መሥዋዕት” የሚያቀርበው “ሁለት እንጀራ” ለምን ነገር ትንቢታዊ ጥላ ነው? (ዘሌ. 23:15-17) [w 98 3/1 ገጽ 13 አን. 21]
13. በዘኍልቁ ምዕራፍ 5 ላይ የተገለጸው ዓይነት ምንዝር በሚፈጸምበት ጊዜ አንዲት ሴት “ጭኗ ይሰልላል” ሲባል ምን ማለት ነው? (ዘኍ. 5:27) [w 84 4/15 ገጽ 29]
14. ማርያምና አሮን ኢትዮጵያዊት በማግባቱ ሙሴን የተቃወሙት ለምን ነበር? (ዘኍ. 12:1)
15. ‘የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ’ ምንድን ነው? (ዘኍ. 21:14)