ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ ጉባኤው ያሉትን እንደ መንግሥትህ ትምጣ እና የአምልኮ አንድነት ያሉ የቆዩ መጽሐፎች።
◼ “ከአምላክ ጋር መሄድ” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ስትገኙ አጠር ያለ ማስታወሻ መያዝ አስፈላጊ መሆኑን አስታውሱ፤ እንዲህ ማድረጋችሁ በዓመቱ ውስጥ በአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ በሚቀርበው የቃል ክለሳ ለመሳተፍ ያስችላችኋል።
◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ከዚያም የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2005 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2005 እና የ2005 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።
◼ በእጅ ያሉት ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2004 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አገልጋዩ (በመንግሥት አዳራሹ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ ደግሞ የጽሑፍ አስተባባሪው) በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶች ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እርሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እውቀት (በኮሪያ ቋንቋ)፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው (በጉጀራቲ፣ በሂንዲና በስፓንኛ) እንዲሁም የወጣቶች ጥያቄ (በጣልያንኛ)።
◼ እንደገና የደረሱን:- እንግሊዝኛ፦ የኢሳይያስ ትንቢት—2፣ ለዘላለም መኖር፣ ራእይ፣ ማመራመር፣ የውዳሴ መዝሙር (ትንሹ)፣ የወጣቶች ጥያቄ፣ በደስታ ኑር፣ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ እና ስንሞት ምን እንሆናለን?