ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 27, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 1 እስከ ታኅሣሥ 27, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አድማጮች የምንናገረውን ነገር በትኩረት እንዲከታተሉ ማድረግ የሚቻልበት ከሁሉ የተሻለው ዘዴ ምንድን ነው? [be ገጽ 218 አን. 2]
2. የንግግሩ መደምደሚያ ግቡን እንዲመታ ሊያሟላቸው የሚገቡትን አምስት ነጥቦች ግለጽ። [be ገጽ 220 አን. 4–ገጽ 221 አን. 4]
3. የምናስተላልፈው መረጃ ትክክለኛ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 224 ሣጥን]
4. ጉባኤው “የእውነት ዓምድና መሠረት” እንደመሆኑ መጠን በስብሰባዎች ላይ ክፍል በምናቀርብበት ወቅት ላገኘነው መብት አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞ. 3:15) [be ገጽ 224 አን. 1-4]
5. የዜና ዘገባዎችን፣ ከሌላ ምንጭ የተወሰዱ ሐሳቦችንና ተሞክሮዎችን በተመለከተ ምሳሌ 14:15ን ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 225 አን. 1]
ክፍል ቁጥር 1
6. ከኖኅ የጥፋት ውኃ በመነሳት አዳም የተፈጠረበትን ጊዜ ወደኋላ ማስላት የሚቻለው እንዴት ነው? [si ገጽ 286 አን. 12]
7. ኢየሱስ አገልግሎቱን የጀመረበትን ጊዜ እንዴት ማወቅ ይቻላል? ምድራዊ አገልግሎቱን ያከናወነው ለሦስት ዓመት ተኩል መሆኑን እንድናምን የሚያደርገን ምን ማስረጃ አለ? [si ገጽ 291 አን. 16]
8. (ሀ) “ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ” የወጣው መቼ ነበር? (ለ) ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ መሲህ ሆኖ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ምን ያህል ዓመታት ያልፋሉ? (ዳን. 9:24-27) [si ገጽ 291 አን. 18-19]
9. ‘ከወንድማችን ጋር ለመታረቅ’ ከልብ የመነጨ ይቅርታ ስንጠይቅ ምን ማድረግ ይኖርብናል? (ማቴ. 5:23, 24 የ1954 ትርጉም) [w02 11/1 ገጽ 6 አን. 1, 5]
10. ከአምላክ የተሰጡንን ሥራዎች በማከናወን ረገድ ከ2 ነገሥት 13:18, 19 ምን ትምህርት እናገኛለን? [w02 12/1 ገጽ 31 አን. 1-2]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. እስራኤላውያን እነርሱ ራሳቸው የማይበሉትን ደሙ ሳይፈስስ የሞተ እንስሳ በአገራቸው ለሚኖር መጻተኛ እንዲሰጡ ወይም ለውጭ አገር ዜጋ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ለምንድን ነው? (ዘዳ. 14:21)
12. ዘዳግም 20:5-7 ምን ትምህርት ይዞልናል?
13. “ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፣ የብድር መያዣ” አድርጎ መውሰድ “የሰውን ነፍስ” መያዣ አድርጎ እንደመውሰድ የተቆጠረው ለምንድን ነው? (ዘዳ. 24:6)
14. እስራኤላውያን ስብ እንዳይበሉ ተከልክለው ስለነበር ‘የጠቦት ስብ’ መብላታቸው ምን ያመለክታል? (ዘዳ. 32:13, 14 የ1954 ትርጉም)
15. አካን የሠራው ኃጢአት በዘመናችን ከተፈጸመው ከየትኛው ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል? (ኢያሱ 7:1-26) [w86 12/15 ገጽ 20 አን. 20]