በዲቪዲ የተዘጋጁ የቪዲዮ ፊልሞች
በደም ምትክ የሚሰጡ ሕክምናዎች—ተከታታይ ጥናታዊ ፊልሞች በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዲቪዲ ሦስት የቪዲዮ ፊልሞችን አካትቶ ይዟል። በደም ምትክ የሚሠራባቸው የሕክምና ዘዴዎች—ቀላል፣ አስተማማኝና ውጤታማ የተባለው ፊልም የተዘጋጀው ለዶክተሮችና ለሕክምና ተማሪዎች በመሆኑ ከሌሎቹ ፊልሞች የበለጠ ሕክምና ሲደረግ የሚያሳዩ ክፍሎች አሉት። በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የተሰኘው ፊልም ደግሞ ከሕክምና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች፣ ለጤና ባለ ሥልጣናት፣ ለማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኞች እንዲሁም ለዳኞች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የሕሙማን ሕጋዊ መብት ችላ ሳይባል የሚያስፈልጋቸውን ሕክምና እንዴት መስጠት እንደሚቻል ያሳያል። ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለው ፊልም ለሁሉም ሰው ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የዲቪዲ ፊልሙ እነዚህን ሦስቱን የእንግሊዝኛ ቪዲዮዎች አጠቃልሎ የያዘ ሲሆን በሩስያኛ፣ በስፓንኛ፣ በጀርመንኛ፣ በጃፓንኛ፣ በጣልያንኛ፣ በፈረንሳይኛና በፖርቱጋል (በብራዚል) ቋንቋ ፊልሞቹን ለመመልከት የሚያስችል ዝግጅትም አለው። እነዚህን የቪዲዮ ፕሮግራሞች ለሐኪማችሁ፣ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪያችሁ፣ ለማያምን የትዳር ጓደኛችሁ ወይም ዘመዳችሁ፣ ለመምህራኖቻችሁ፣ ለሥራ ባልደረቦቻችሁ እንዲሁም አብረዋችሁ ለሚማሩት ልጆች ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ።