የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/04 ገጽ 5
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 12/04 ገጽ 5

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ፦ ታላቅ ሰው። በአማራጭነት መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ወይም ለዘላለም መኖር የተባሉትን መጽሐፎች ማበርከት ይቻላል። ጥር:- “ነቅተህ ጠብቅ!” የተባለውን ብሮሹር ለማሰራጨት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ። የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ። መጋቢት:- “ነቅተህ ጠብቅ!”

◼ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች በትልቅ ወረቀት ጽፋችሁ እስከ ታኅሣሥ 31, 2004 ድረስ ልትልኩልን ትችላላችሁ:- 1) ስም 2) ዕድሜ 3) የተጠመቅክበት ቀን 4) የጋብቻ ሁኔታ [ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት] 5) ለማገልገል የምትችልባቸው ወራት [ከመጋቢት እስከ ግንቦት?] 6) የምትናገራቸው ቋንቋዎች 7) አመልካቹ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ አዘውትሮ የሚካፈል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት የድጋፍ ሐሳባቸውን ካሰፈሩ በኋላ ይፈርሙበታል።

◼ ለ2005 የመታሰቢያ በዓል የሚያገለግል የመጋበዣ ወረቀት (ጉባኤው በሚመራበት ቋንቋ) በቅርቡ ለጉባኤዎች ይላካል።

◼ የመታሰቢያው በዓል ትልቅ ግምት የሚሰጠው ከመሆኑ አኳያ የሽማግሌዎች አካል ንግግሩን የሚያቀርበውን ወንድም ሲመድብ ብቃት ያለውን ሽማግሌ ይመርጣል እንጂ በተራ እንዲዳረስ ወይም በየዓመቱ አንድ ሽማግሌ ብቻ እንዲያቀርብ ማድረግ የለበትም። ንግግሩን ማቅረብ የሚችል ቅቡዕ ሽማግሌ ካለ እርሱ ሊመደብ ይገባል።

◼ በ2006 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል።

◼ ከሰኔ 27, 2005 ጀምሮ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለው መጽሐፍ ይሆናል።

◼ “የሐኪሞችን ችግር ተረዱላቸው” የሚል ርዕስ ያለው የመጋቢት 2005 ንቁ! ሕመምተኞች ከሐኪሞቻቸው ጋር ይበልጥ ለመግባባት እንዲችሉ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ሆኖም መጽሔቱ አንዳንድ ሐኪሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ተስፋ የማረካቸው ለምን እንደሆነም ጭምር ስለሚያብራራ ለሐኪሞቹ ለራሳቸውም ጠቃሚ እንደሚሆን አያጠራጥርም። የዚህን መጽሔት ተጨማሪ ቅጂዎች በማዘዝ ለሐኪሞቻችሁና ለሌሎች የጤና ባለሞያዎች ለማዳረስ ጥረት ማድረግ ትችላላችሁ። ጉባኤዎች ተጨማሪ መጽሔቶች ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ትእዛዛቸውን ለቅርንጫፍ ቢሮው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ