የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/05 ገጽ 1
  • የይሖዋ ቀን ቀርቧል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ቀን ቀርቧል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ መንግሥት ተቋቁሟል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • “ነቅታችሁ ጠብቁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ​—ክፍል 7
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 5/05 ገጽ 1

የይሖዋ ቀን ቀርቧል

1 ክርስቲያኖች አሁን ያለውን ሥርዓት አጥፍቶ ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ምድር የሚያመጣውን የይሖዋን ቀን መምጣት በናፍቆት ይጠባበቃሉ። (2 ጴ⁠ጥ. 3:​12, 13 የግርጌ ማስታወሻ) የይሖዋ ቀን የሚመጣበትን ጊዜ ስለማናውቅ ነቅተን መጠባበቅና ሌሎችም እንዲህ እንዲያደርጉ መርዳት ይኖርብናል። (ሕዝ. 33:​7-9፤ ማቴ. 24:​42-44) በአምላክ ትንቢታዊ ቃል ላይ ማሰላሰላችን “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ” እንደሆነ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።​—⁠ሶፎ. 1:​14

2 የዓለም ኃያላን መንግሥታት ቅደም ተከተል:- ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ 17:​9-11 ላይ የጠቀሳቸው “ሰባት ነገሥታት” በተከታታይ የሚነሱ ሰባት የዓለም ኃያላን መንግሥታትን ያመለክታሉ። ዮሐንስ ቀጥሎ የገለጸው “ስምንተኛው ንጉሥ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የሚያመለክት ነው። ከአሁን በኋላ ሌሎች የዓለም ኃያላን መንግሥታት እንደሚመጡ መጠበቅ ይኖርብናል? በፍጹም፣ ምክንያቱም ትንቢቱ ይህ ስምንተኛ ንጉሥ ‘ወደ ጥፋቱ እንደሚሄድ’ የገለጸ ሲሆን ከስምንተኛው በኋላ የሚነሳ ሌላ ምድራዊ ንጉሥ አልተጠቀሰም። ታዲያ ይህ ትንቢት በጊዜ ሂደት ውስጥ የት ቦታ ላይ እንዳለን ለማስተዋል አስችሎሃል?

3 ዳንኤል 2:​31-45 ስለ ይሖዋ ቀን መምጣት ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳናል። በትንቢቱ ውስጥ የተገለጸው ናቡከደነፆር በሕልሙ የተመለከተው ግዙፍ ምስል በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረቁትን የዓለም ኃያላን መንግሥታት ያመለክታል። በምስሉ የተወከሉት የዓለም ኃያላን መንግሥታት በሙሉ አልፈዋል። በዛሬው ጊዜ የሚገዛው ኃያል መንግሥት ማነው? በሕልም በታየው ምስል ላይ በእግር የተመሰለው መንግሥት ነው። ከዚህ በኋላ ምን እንደሚከሰት ትንቢቱ በግልጽ አስቀምጦታል። የሰው ልጅ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ‘ፈጽሞ ለማይፈርሰው መንግሥት’ ቦታውን ይለቅቃል። ይህ ትንቢት የይሖዋ ቀን ምን ያህል እንደቀረበ የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ መገንዘብ ችለሃል?

4 ተጨማሪ ማስረጃ:- የይሖዋ ቀን መቅረቡን የሚያመለክተውን ተጨማሪ ማስረጃ እኛ ራሳችን የዓይን ምሥክሮች ሆነን አይተነዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ “በመጨረሻው ዘመን” ስለሚኖረው ማኅበረሰብ ባሕርያት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዳገኘ በግልጽ እየተመለከትን ነው። (2 ጢ⁠ሞ. 3:​1-5) እኛም መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት በዓለም ዙሪያ በሚከናወነው የስብከት ሥራ ላይ እየተካፈልን ነው። (ማቴ. 24:​14) “እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል” እያለ የሚያውጀውን መልአክ በመምሰል አገልግሎታችንን በጥድፊያ ስሜት እናከናውን።​—⁠ራእይ 14:​6, 7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ