ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች፤ ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ፤ ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች።
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ በዚህ ዓመት ለሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ የሚሆኑ ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች ከጽሑፎች ጋር ይላኩላችኋል። ጉባኤው ተጨማሪ ካርድ ካስፈለገው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርበታል። የካርድ መያዣ ፕላስቲክ ማግኘት የሚፈልግ ሰው ካለ ትእዛዙ መላክ ይኖርበታል።
◼ በ2005 ለሚደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች የወጣ ፕሮግራም:-
መስ. 16-18 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ*3ሀ, 1ሀ ኣማርኛ/ የምልክት ቋንቋ
መስ. 23-25 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ2ሀ, 7ሀ አማርኛ
መስ. 30-ጥቅ. 2 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ5ሀ, 1ለ አማርኛ
ጥቅ. 7-9 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ5ለ እንግሊዝኛ
ጥቅ. 14-16 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ6ሀ, 9ሀ አማርኛ
መስ. 23-25 ወረዳ ቁ.ጅማ1ሐ, 8ሐ አማርኛ
መስ. 23-25 ወረዳ ቁ.ድሬዳዋ7ሐ አማርኛ
መስ. 30-ጥቅ. 2 ወረዳ ቁ.ባህር ዳር6ለ አማርኛ
መስ. 30-ጥቅ. 2 ወረዳ ቁ.ሻሸመኔ4ሀ አማርኛ
ጥቅ. 7-9 ወረዳ ቁ.ሶዶ9ለ, 9ሐ አማርኛ
ጥቅ. 7-9 ወረዳ ቁ.ይርጋለም10 ሲዳማ
ጥቅ. 14-16 ወረዳ ቁ.አምቦ8መ ኦሮምኛ
ጥቅ. 14-16 ወረዳ ቁ.ደሴ2ለ አማርኛ
ጥቅ. 21-23 ወረዳ ቁ.ነቀምቴ8ሀ አማርኛ
ጥቅ. 21-23 ወረዳ ቁ.ናዝሬት7ለ አማርኛ
ጥቅ. 21-23 ወረዳ ቁ.አለታ ወንዶ4ለ አማርኛ
ጥቅ. 28-30 ወረዳ ቁ.ጊምቢ8ለ ኦሮምኛ
ጥቅ. 28-30 ወረዳ ቁ.ሶዶ3ለ ወላይትኛ
ጥቅ. 28-30 ወረዳ ቁ.መቀሌ2ሐ ትግርኛ
በአዲስ አበባ የሚደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች ሁሉ የሚካሄዱት በቅርንጫፍ ቢሮው ግቢ ውስጥ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ነው።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችንና የጸሐፊዎችን ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ ይኖርበታል።
◼ አዲስ የደረሰን ጽሑፍ:- አማርኛና እንግሊዝኛ፦ የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ።