ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ነቅተህ ጠብቅ! ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “መጽሐፍ ቅዱስን መመሪያችን አድርገን ልንጠቀምበት የሚገባው ለምንድን ነው?” የሚል ይሆናል።
◼ ለተወሰነ ጊዜ በጉባኤ ያልነበሩ አስፋፊዎች ተመልሰው ሲመጡ የጉባኤ ጸሐፊዎች የሚከተለውን መመሪያ በሥራ እንዲያውሉ እንጠይቃለን። አስፋፊዎች በሆነ ወቅት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን ባለመመለሳቸው ምክንያት ካርዳቸው ላይ አለመመዝገቡን ካያችሁ እንዲሰጧችሁ መጠየቃችሁ ተገቢ ነው። ካርዳቸው ላይ ሳይሞላ የቀረው የሁለት ወይም የሦስት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ከሆነ የእያንዳንዱን ወር ሪፖርት በተናጠል መመለስ ይኖርባቸዋል። የተለያዩ ወሮችን ሪፖርት አንድ ላይ ደምሮ መመለሱ ትክክል አይደለም። እነዚህ ሳይላኩ የቀሩ ሪፖርቶች በጉባኤው የአስፋፊዎች ቁጥርም ሆነ በሌሎቹ አኃዞች ላይ ተደምረው ከቀጣዩ ወር የጉባኤ ሪፖርት (S-1) ጋር መላክ አለባቸው። የአገልግሎት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት የዘገዩ ሪፖርቶችን በሙሉ መላኩ አስፈላጊ ነው።
◼ ለዘወትር አቅኚነት የሚቀርብ ማመልከቻ፣ አቅኚው መጀመር ከሚፈልግበት ቀን ቢያንስ ከ30 ቀናት በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላኩ አስፈላጊ ነው። የጉባኤው ጸሐፊ የማመልከቻ ቅጾቹ በሚገባ መሞላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን ገምተው ለማወቅ መጣርና ይህን ቀን መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊ ይህን ቀን የጉባኤ አስፋፊ ካርድ (S-21) ላይ ሊመዘግበው ይገባል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች በጉባኤያችሁ ያለ እያንዳንዱ የዘወትር አቅኚ የዘወትር አቅኚ የሹመት ደብዳቤ (S-202) እንዳለው አረጋግጡ። ከሌለው ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላላችሁ።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አረብኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ ቻይንኛ፦ ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን? (T-19)፤ እንግሊዝኛ፦ የ2005 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2004 መጠበቂያ ግንብ ጥራዝ፣ በሲዲ የተዘጋጀ የ2004 የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት፤ ፈረንሳይኛ፦ የ2005 የዓመት መጽሐፍ፣ የተደራጀ ሕዝብ፣ የ2004 መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞች።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች:- ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ መያዣ ፕላስቲክ፣ የአገልግሎት ክልል ካርድ መያዣ ፕላስቲክ፤ አማርኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ የዳንኤል ትንቢት፣ የኢሳይያስ ትንቢት—2፣ የተደራጀ ሕዝብ፣ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? (T-22)፣ የቪዲዮ ካሴት:- እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?፤ አረብኛ፦ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም፤ እንግሊዝኛ፦ ነቅተህ ጠብቅ!፣ አምላክን አምልክ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ ክርኤተር፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ የመዝሙር መጽሐፍ (ትንሹ)፣ ጉድ ኒውስ ፎር ኦል ኔሽንስ፤ ፈረንሳይኛ፦ የወጣቶች ጥያቄ፣ ነቅተህ ጠብቅ!፤ ጣሊያንኛ፦ የወጣቶች ጥያቄ፤ ትግርኛ:- ነቅተህ ጠብቅ!