ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ነቅተህ ጠብቅ! ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች፤ ኅዳር:- እውቀት።
◼ የጥቅምት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ግሩም አጋጣሚ ይከፍታል።
◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ ለሰዎች ደብዳቤ ስትጽፉ የላኪ አድራሻ ላይ የቅርንጫፍ ቢሮውን አድራሻ መጠቀም እንደሌለባችሁ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን። ይህም ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች፣ በቤታቸው ላላገኛችኋቸው ወይም ከእኛ ርቀው ለሚኖሩ ሰዎች ምሥክርነት ለመስጠት ሲባል የሚላኩ ደብዳቤዎችን ወይም ጽሑፎችን ያካትታል። አንድ አስፋፊ አገልግሎቱ በግሉ ለአምላክ የሚያቀርበው አምልኮ እንደመሆኑ መጠን የግሉን የፖስታ አድራሻ ለመጠቀም ሊመርጥ ይችላል። (ማቴ. 28:19, 20፤ ሮሜ 10:14, 15) ይሁን እንጂ የራሱን አድራሻ መስጠት ጥበብ እንዳልሆነ ከተሰማው የራሱን ስም በመጻፍ የጉባኤውን የፖስታ አድራሻ መስጠት ይችላል።—በኅዳር 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
◼ በእጅ ያሉ ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2005 ላይ ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር የጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እርሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2006 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2006 እና የ2006 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።