የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/05 ገጽ 7
  • ያለ ቃል የሚሰጥ ምሥክርነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያለ ቃል የሚሰጥ ምሥክርነት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • መልካም ሥራዎች ይሖዋን ያስከብራሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ዕብራውያን 4:12—“የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • የአምላክ መንፈስ እንዲመራችሁ ትፈቅዳላችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 8/05 ገጽ 7

ያለ ቃል የሚሰጥ ምሥክርነት

1 የይሖዋ ግዑዝ ፍጥረታት አንደበት ባይኖራቸውም እንኳ ስለማይታዩት ባሕርያቱ ብዙ ይናገራሉ። (መዝ. 19:1-3፤ ሮሜ 1:20) እኛም በተመሳሳይ የምናሳየው መልካም ምግባር፣ ክርስቲያናዊ ባሕርይና ልከኛ አለባበስ ያለ ቃል ምሥክርነት መስጠቱ አይቀርም። (1 ጴጥ. 2:12፤ 3:1-4) እያንዳንዳችን በባሕርያችን አማካኝነት “በሁሉም መንገድ የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት ይወደድ ዘንድ” ምኞታችን ሊሆን ይገባል።—ቲቶ 2:10

2 ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እንዴት ማስዋብ ይችላሉ? ይህ ሊሆን የሚችለው በአምላክ ቃል መመሪያና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው። (መዝ. 119:105፤ 143:10) የአምላክ ቃል “ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ ስለታም ነው።” (ዕብ. 4:12) የአምላክ ቃል ልባችን ውስጥ ዘልቆ በመግባት አዲሱን ሰውነት እንድንለብስ ያስችለናል። (ቆላ. 3:9, 10) መንፈስ ቅዱስ ደግሞ እንደ ቸርነት፣ በጎነት፣ የዋህነትና ራስን መግዛት የመሳሰሉ ግሩም ባሕርያትን እንድናፈራ ይረዳናል። (ገላ. 5:22, 23) የአምላክ ቃል እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንዲችሉ በግለሰብ ደረጃ ፈቅደናል?—ኤፌ. 4:30፤ 1 ተሰ. 2:13

3 ሰዎች ይመለከቱናል:- ይሖዋ ባወጣቸው የአቋም ደረጃዎች ሕይወታችንን ስንመራም ይሁን የእርሱን ባሕርያት ለማንጸባረቅ ስንጥር ሌሎች መመልከታቸው አይቀርም። ለምሳሌ ያህል ቁመቱ አጭር በመሆኑ ምክንያት የሥራ ባልደረቦቹ ያሾፉበት የነበረን አንድ ሰው እንመልከት። አብራው የምትሠራው አንዲት እህት ግን ለዚህ ሰው ሁልጊዜ አሳቢነትና አክብሮት ታሳየው ነበር። ይህ ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች የተለየች የሆነችበትን ምክንያት እንዲጠይቃት ገፋፋው። እህት ጥሩ ምግባር እንዲኖራት የረዳት የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በተግባር ማዋሏ መሆኑን ገለጸችለት። በተጨማሪም ግሩም የሆነውን የመንግሥቱን ተስፋ አካፈለችው። ይህ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመረና እድገት አድርጎ ተጠመቀ። ወደ ትውልድ አገሩ ሲመለስ ባሳየው መልካም ምግባር ዘመዶቹ በመነካታቸው ብዙዎቹ እውነትን ሊቀበሉ ችለዋል።

4 በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት አሊያም ደግሞ ለዘመዶቻችንና ለጎረቤቶቻችን የምናሳየው መልካም ምግባር ከስብከት ሥራችን ጋር ተዳምሮ ሰዎች አምላክን እንዲያከብሩ የሚገፋፋቸው እንዲሆን ጥረት እናድርግ።—ማቴ. 5:16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ