ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- ነቅተህ ጠብቅ! ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች፤ ኅዳር:- እውቀት፤ ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው።
◼ የጥቅምት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ግሩም አጋጣሚ ይከፍታል።
◼ በ2006 የአገልግሎት ዓመት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉባኤውን በሚጎበኝበት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ በጉብኝቱ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ከዘወትር አቅኚዎች ጋር በሚያደርገው ስብሰባ የመጀመሪያ ክፍል ላይ እንዲገኙ ተፈቅዶላቸዋል። አቅማችሁ የሚፈቅድ ሁሉ ከዚህ ልዩ ዝግጅት እንድትጠቀሙ እናበረታታችኋለን።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 11 ላይ የወጣውን ሐሳብ በ2005/06 ከሚደረገው የወረዳ ስብሰባ ጋር በተያያዘ የምንጠቀምበት ስለሆነ በጥሩ ሁኔታ ልትይዙት ይገባል።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማሳወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት ጽሑፎች የትኞቹ እንደሆኑ እባካችሁ አትርሱ።
◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-23 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።