የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/05 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 11/05 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር:- እውቀት፤ ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው፤ ጥር:- ነቅተህ ጠብቅ! የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ።

◼ ታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።

◼ ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራና ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ ቼክ ፈርመው በጉባኤ የአስተዋጽኦ ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩ ካሉ ክፈል በሚለው የቼኩ ክፍት ቦታ ላይ መጻፍ ያለባቸው “የይሖዋ ምሥክሮች” ወይም “Yeyihowa Misikiroch” ብለው ነው።

◼ በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የሚለውን የቪዲዮ ፊልም በጥር ወር የአገልግሎት ስብሰባ ላይ እንከልሳለን። የቪዲዮ ክሩን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።

◼ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች:- ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት አዳዲስ ክልሎችን ለመሸፈን በሚደረገው ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች ጽፋችሁ በጉባኤያችሁ የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል እንድትልኩ ትጠየቃላችሁ። እባካችሁ እነዚህን መረጃዎች አካትቱ:- 1) ስም፣ 2) የትውልድ ዘመን፣ 3) የጥምቀት ቀን፣ 4) የጉባኤው ስም፣ 5) የጋብቻ ሁኔታ፣ 6) በአንተ ሥር የሚተዳደሩ ሰዎች ካሉ ጥቀስ፣ 7) የምትናገራቸው ቋንቋዎች፣ 8) ዘመቻው ሲያበቃ በልዩ አቅኚነት መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ግለጽ። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የአመልካቹን ብቃት በተመለከተ ሐሳብ ካሰፈረ በኋላ ደብዳቤውን እስከ ታኅሣሥ 31, 2005 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲደርስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ይልካል። የሚያስፈልጉት ቀናተኛ ሰባኪዎች እንዲሁም ትጉህና ውጤታማ ሠራተኞች ናቸው። በአገልግሎት ጠንካራ ጎኑ የትኛው ነው? ከቤት ወደ ቤት በመሄድ ክልል የሚሸፍን ቀናተኛ ሰባኪ ነው? ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ቁም ነገረኛ ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በመምራት ረገድ ጥሩ አስተማሪ ነው? የመንፈስ ፍሬ በማፍራቱ ምክንያት ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መሥራት የሚችል ነው? ግለሰቡ ለዚህ ቅዱስ የአገልግሎት መብት ይበቃል ትላላችሁ? አመልካቹ ብቁ አይደለም ብላችሁ ከወሰናችሁ ማመልከቻውን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አያስፈልግም። ከዚህ ይልቅ ውሳኔያችሁን ከነገራችሁት በኋላ በደግነት ምክር ስጡት። ውሳኔ ላይ ስንደርስ ብቁ ሆነው ያገኘናቸውን ወንድሞችና እህቶች በጉባኤያቸው በኩል እናሳውቃቸዋለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ