የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/06 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 1/06 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- ነቅተህ ጠብቅ! የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው አዲስ መጽሐፍ የሚበረከት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት አድርጉ።

◼ የሚያዝያ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።

◼ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ከመጋቢት 2006 ጀምሮ የሚሰጡት አዲስ የሕዝብ ንግግር “አሁንም ሆነ ለዘላለም ሰላማዊ ሕይወት መኖር ትችላላችሁ!” የሚል ርዕስ አለው።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን እንዲያከብር እናበረታታለን። ይሁንና አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ለማድረግ ላይሳካላችሁ ይችላል። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚያደርጉ በርካታ ጉባኤዎች ካሉ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ሁሉም ከዝግጅቱ ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ከተቻለ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንና መጫንን ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።

◼ ወደ ሌላ አገር በምትጓዙበት ወቅት በዚያ በሚደረገው የጉባኤ፣ የወረዳና የልዩ ወይም የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ስብሰባዎች የሚካሄዱበትን ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ በዚያ አገር ለሚካሄደው ሥራ አመራር ለሚሰጠው ቅርንጫፍ ቢሮ መጻፍ ይኖርባችኋል። የተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ በቅርብ በወጣው የዓመት መጽሐፍ የመጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ