ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው አዲስ መጽሐፍ የሚበረከት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመርም ልዩ ጥረት አድርጉ። ሚያዝያና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
◼ የሚያዝያ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ረቡዕ ሚያዝያ 12, 2006 ነው። ጉባኤያችሁ ረቡዕ ዕለት ስብሰባ ያደርግ ከሆነ ይህን ስብሰባ የመንግሥት አዳራሹ ነጻ ወደሚሆንበት ሌላ ቀን ማዛወር ይኖርባችኋል። እንዲህ ማድረግ ካልተቻለና የአገልግሎት ስብሰባው ሳይቀርብ ከቀረ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑትን ክፍሎች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ማካተት ይቻላል።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚቀርበው የ2006 ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?” የሚል ይሆናል። ይህ ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 30 ይቀርባል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 30, 2006 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።
◼ ጉባኤዎች አዳዲስ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች እንደደረሷቸው አስፋፊዎች እንዲወስዱ ማድረግ ይኖርባቸዋል። እንደዚህ መደረጉ አስፋፊዎች መጽሔቶቹን በአገልግሎት ላይ ከማበርከታቸው በፊት ማንበብ እንዲችሉ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። የመንግሥት አገልግሎታችንም ቢሆን ወደ ጉባኤው እንደደረሰ ለአስፋፊዎች ሊሰጥ የሚገባ ሲሆን ይህንንም በመጽሐፍ ጥናት ላይ ማድረግ ይቻላል።
◼ በግንቦት ወር የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ኖኅ—አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም እንከልሳለን። የቪዲዮ ክሩን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት ጽሑፎች የትኞቹ እንደሆኑ እባካችሁ አትርሱ።
◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የልዩና የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት የዚያን አገር ሥራ በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።