ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- እውቀት፤ የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሚያዝያ:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ።
◼ ከመጋቢት 4 ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “ወደ አምላክ አዲስ ዓለም ለመግባት ብቃቱ የሚኖራቸው እነማን ናቸው?” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።
◼ በሚያዝያ ወር ውስጥ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? የተሰኘውን ፊልም እንከልሳለን። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ በቻይንኛ የሚታተሙት ጽሑፎቻችን የሚዘጋጁት በሁለት ዓይነት ፊደላት ነው። ከሆንግ ኮንግ እና ከታይዋን የሚመጡ ሰዎች በአብዛኛው የሚያነቡትን የጥንቱን ቻይንኛ “Chinese” (CH) ብለን የሰየምነው ሲሆን ሌሎች ብዛት ያላቸው ቻይናውያን ግን ቀለል ባለ መልኩ የተጻፈውን ማለትም “Simplified Chinese” (CHS) የምንለውን ያነብባሉ። አንድ ሰው የሚያነበው የፊደል ዓይነት ከሚናገረው ቋንቋ ለምሳሌ ያህል ከካንቶኒዝ፣ ከማንዳሪን ወይም ከሌላ ቀበሌኛ ጋር ተዛማጅነት ስለሌለው እርሱ የሚያነበው በየትኛው ፊደል የተጻፈውን እንደሆነ ብንጠይቀው ጥሩ ነው። ሁኔታውን ለማወዳደር ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ምሥራች የሚለውን ቡክሌት ገጽ 13-14 መመልከት ይቻላል። በዚህ መንገድ በምትፈልጉት ፊደል የተጻፈውን ጽሑፍ ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ሰኞ፣ ሚያዝያ 2 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ለሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን እንዲያከብር እናበረታታለን። ይሁንና አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ለማድረግ ላይሳካላችሁ ይችላል። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚያደርጉ በርካታ ጉባኤዎች ካሉ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ሁሉም ከዝግጅቱ ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ከተቻለ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ 40 ደቂቃ ያህል እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንና መጫንን ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች በጉባኤያችሁ ያለ እያንዳንዱ የዘወትር አቅኚ በጉባኤው ፋይል ውስጥ የዘወትር አቅኚ የሹመት ደብዳቤ (S-202) እንዳለው አረጋግጡ። በፋይል ውስጥ የማይገኝ ከሆነ ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላላችሁ።
◼ መጽሔት ዘግይቶ የሚደርሳቸው ጉባኤዎች የዓመቱን ጥቅስ የሚያብራራው የታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብ እትም እንደደረሳቸው ለማጥናት ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
◼ አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ወይም ጉባኤዎች ለራሳቸው የመንግሥት አዳራሽ ከሚያደርጉት መዋጮ ሌላ በዓለም ዙሪያ ለሚደረገው የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ መዋጮ ማድረግ ይፈልጉ ይሆናል። ሌሎች የመንግሥት አዳራሾችን ለመገንባት የሚደረጉትን እንዲህ ያሉ መዋጮዎች “ለዓለም አቀፉ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ” ብሎ መላክ ይቻላል። በገንዘብ መላኪያ ቅጽ (S-20) ላይ በሚገኘው ክፍት ቦታ ላይ ለዚህ ዓላማ መላኩ መገለጽ ይኖርበታል።