ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ የካቲት 26, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 1 እስከ የካቲት 26, 2007 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. በንግግራችን ላይ የትምህርቱን ጠቀሜታ ግልጽ ማድረግ ያለብን መቼ ነው? ይህስ በምን መልኩ መደረግ አለበት? [be ገጽ 158 አን. 2-4]
2. ሌሎች የምናቀርበውን ትምህርት ጠቀሜታ እንዲያስተውሉ መርዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንንስ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 159 አን. 2-3]
3. ትክክለኛ ቃላት መምረጣችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 160]
4. የተለያዩ ቃላትን በትክክለኛ መንገድ ለመጠቀም ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 161 አን. 5-6፤ ገጽ 162 አን. 1, 4]
5. ሐሳብን በአእምሮ አቀናብሮ ወይም በወረቀት ላይ አስተዋጽኦ አዘጋጅቶ መናገር ምን ጥቅሞች አሉት? [be ገጽ 166 አን. 1-3]
ክፍል ቁጥር 1
6. በንባብ የሚቀርብ ክፍል መዘጋጀት ምን ነገሮችን ይጨምራል? [be ገጽ 43 አን. 2, 4]
7. ይሖዋ ለመልካም ነገር ያለውን ፍቅርና ለክፉ ነገር ያለውን ጥላቻ መኮረጅ የምንፈልግ ከሆነ ምን ማድረጋችን ወሳኝ ነው? (ዕብ. 5:14) [w05 1/1 ገጽ 9 አን. 11]
8. አምላክ የወሰደው እርምጃ ፍትሐዊ ወይም ትክክል መሆኑን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብናነብ ምን ማስታወስ ይኖርብናል? [w05 2/1 ገጽ 24 አን. 7]
9. በአምላክ ሕግና በሰዎች ትእዛዝ መካከል ቅራኔ ቢፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል? [w05 4/15 ገጽ 12 አን. 9]
10. ኢሳይያስ በመሲሑ ስለሚመራው መንግሥትና መንገድ ጠራጊ ስለሆነው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ጎላ አድርጎ የገለጸው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 31 አን. 35]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በኢሳይያስ 25:7 ላይ የተጠቀሰው “መጋረጃ” እና “መሸፈኛ” ምንድን ነው?
12. ሰዎች ይሖዋን ‘ሊያዩትና’ ‘ሊሰሙት’ የሚችሉት እንዴት ነው? (ኢሳ. 30:20, 21)
13. እውነት ወይስ ሐሰት:- ሕዝቅያስ በኢሳይያስ 38:3 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ጸሎት እንዲያቀርብ የገፋፋው ብቸኛ ምክንያት ረጅም ዘመን ለመኖር ያለው ፍላጎት ነበር።
14. እስራኤላውያን የይሖዋ ምሥክሮች ሆነው ያገለገሉት እንዴት ነበር? እኛስ እነርሱን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? (ኢሳ. 43:10)
15. በኢሳይያስ 52:11, 12 ትንቢታዊ ጥላ መሠረት ‘የይሖዋን ዕቃ የሚሸከሙ’ ሰዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?