ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ጥቅምት:- መጽሔቶችና T-27 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል!)።
◼ መስከረም ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ለመሆኑ ማረጋገጫው ምንድን ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ይሆናል።
◼ ለዘወትር አቅኚነት የሚቀርብ ማመልከቻ፣ አስፋፊው አቅኚነት መጀመር ከሚፈልግበት ቀን ቢያንስ ከ30 ቀናት በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላኩ አስፈላጊ ነው። የጉባኤው ጸሐፊ የማመልከቻ ቅጾቹ በሚገባ መሞላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን ገምተው ለማወቅ መጣርና ይህን ቀን መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊ ይህን ቀን የጉባኤ አስፋፊ ካርድ (S-21) ላይ ሊመዘግበው ይገባል።
◼ በእጅ ያሉ ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2007 ላይ ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር የጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።