ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር:- ነቅተህ ጠብቅ! ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው ወይም ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ጥር:- እውቀት ወይም ነቅተህ ጠብቅ! የካቲት:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
◼ የታኅሣሥ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ለዓለም አቀፉ ሥራ የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ ቼክ ፈርመው ሣጥን ውስጥ የሚከትቱ ወይም ቼኮችን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮ የሚልኩ ሁሉ ገንዘቡ ለ“የይሖዋ ምሥክሮች” (Yeyihowa Misikiroch) የሚከፈል መሆኑን ማመልከት ይኖርባቸዋል።
◼ አስፋፊዎች እስከ አሁን ድረስ የሕክምና መመሪያ ካርዳቸውን ሞልተው ካላጠናቀቁ አሁን እንዲሞሉ እናበረታታቸዋለን። ይህ ካርድ ደም እንደማትወስዱ ያላችሁን አቋም ያስከብርላችኋል። እንደ አስፈላጊነቱ ሽማግሌዎች በግል ሊረዷችሁ ይችላሉ።—የኅዳር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችንን አባሪ ተመልከት።
◼ አስፋፊዎች ከአሁን በኋላ በወር ውስጥ ለመሩት እያንዳንዱ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የጥናት ሪፖርት (S-3) የተባለውን ቅጽ መሙላት አያስፈልጋቸውም። ይሁን እንጂ በወሩ ውስጥ የመሯቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ብዛት የመስክ አገልግሎት ሪፖርት (S-4) በሚባለው ቅጽ ላይ በተዘጋጀው ቦታ መጻፍ ይኖርባቸዋል። ከአሁን በኋላ S-3 የተባለው ቅጽ የሚያገለግለው የጉባኤ ተሰብሳቢዎችን ቁጥር ለመመዝገብ ብቻ ይሆናል።